የነፃው ፕሬስ አሣታሚ ድርጅቶች ለፍ/ቤት ተቃውሟቸውን አቀረቡ

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. December 26, 2008)፦ “ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለመናድ” በሚል፣ በእነ ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል የክስ መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት፤ “ሰርካለም አሣታሚ ድርጅት” 120 ሺህ ብር፣ “ሲሳይ የሕትመትና የማስታወቂያ ድርጅት” 100 ሺህ ብር የተጣለባቸውን ቅጣት እንዲከፍሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ለቀረበባቸው አፈፃፀም ክስ፣ ጉዳዩ በይቅርታ የተቋጨ በመሆኑ ልንጠየቅ አይገባም ሲሉ መከራከሪያቸውን ለፍርድ ቤት አቀረቡ። ፍርድ ቤቱ መከራከሪያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ደርሶት ለሰኞ መልስ እንዲሰጥበት አዟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ደህንነት አደጋ ላይ ነው

W/t Birtukan Mideksaበቀን አራት መኪኖች ይከታተሏቸዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. December 26, 2008)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑንና በየቀኑ አራት መኪኖች እንደሚከታተሏቸው የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢቴቪ የስድስት አሸናፊ ተጫራቾችን ውል ሰረዘ

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. December 26, 2008)፦ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት፣ የተለያዩ ዝግጅቶችን በስፖንሰሮች አሠርቶ ለማስተላለፍ አውጥቶት በነበረው ጨረታ፣ የመጨረሻ አሸናፊ ካደረጋቸው 11 ድርጅቶች ውስጥ፣ የስድስቱን በበጀት እጥረት ምክንያት መሰረዙን እንዳስታወቃቸው ምንጮች ጠቆሙ። ኢቴቪ ድርጅቶቹ ለሥራ ያወጡትን ወጪ በድርድር ካሣ ለመክፈል ጠይቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢንተርኔት አገልግሎት የንግዱ ማኅበረሰብ ተማረረ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. December 24, 2008)፦ ካለፈው ሣምንት አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም እንዳስቸገራቸውና በሥራቸው ላይ እንቅፋት እንደተፈጠረባቸው በአዲስ አበባ የሚኖሩ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ምሬታቸውን ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርቲስት ምኒልክ ወስናቸው ዛሬ አረፈ

Artist Menilik Wossenachew, (1941 - 2008)1933 - 2001 ዓ.ም.

Ethiopia Zare (ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. December 24, 2008)፦ እውቁና አንጋፈው ድምፃዊ ምኒልክ ወስናቸው ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ዘገበ። ነገ የቀብሩ ስነሥርዓት ይፈፀማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

W/t Birtukan Mideksa"በሦስት ቀን ውስጥ ቃልሽን አርሚ፤ ካልሆነ እስር ቤት ትገቢያለሽ" ፌደራል ፖሊስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. December 23, 2008)፦ የአንድነት ለዲሞክራሰና ለፍትህ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በፌደራል ፖሊስ ተወስደው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርቲስት ቴዲ አፍሮ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቀረበ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. December 20, 2008)፦ ከዘጠኝ ወራቶች በላይ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተል የቆየው ቴዎድሮስ ካሳሁን ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. በዋለው የከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ለስድስት ዓመታት የእስርና የ18 ሺህ ብር ቅጣት ከተወሰነበት በኋላ የይግባኝ ማመልከቻውን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረቡ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ታምራት ላይኔ ነገ፣ ዓርብ ይፈታሉ

Ato Tamerat LayneEthiopia Zare (ኀሙስ ታህሳስ 9 ቀን 2001 ዓ.ም. December 18, 2008)፦ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ፤ ለ12 ዓመታት በእስር ከቆዩ በኋላ ነገ ጠዋት ዓርብ ታህሳስ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. ቃሊቲ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንደሚለቀቁና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚቀላቀሉ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለፁ።  ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቫንኩቨሩ ውይይት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

Teklemikael Abebe (L), Azale Desta (R)Ethiopia Zare (እሁድ ታህሳስ 5 ቀን 2001 ዓ.ም. December 14, 2008)፦ ትላንት ቅዳሜ ዲሴምበር 13 ቀን 2008 እ.ኤ.አ. በቫንኩቨር ካናዳ "በመጭው ምርጫ ሀገር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች ምን ማድረግ አለባቸው? በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንስ ድርሻና ተሳትፎ ምን ድረስ ነው?" በሚል የተካሄደው ህዝባዊ ውይይት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...