”ከእስር የተፈታነው በሀገር ሽማግሌዎች ጥረት ነው” ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ
Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 3 ቀን 2001 ዓ.ም. December 12, 2008)፦ ምርጫ 97ን ተከትሎ በመንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፣ በተነሳ ረብሻ እስር ቤት ገብተው የነበሩት የቀድሞ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ተ/ም/ሊቀመንበርና የአሁኑ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር የተፈቱበትን ሁኔታ አስመልክቶ፣ ”ይቅርታ አልጠየቅንም የሚል ይዘት ያለው መግለጫ በአውሮፓ ሰጥተዋል” በሚል ጉዳዩን እንዲያብራሩ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁና በአሁኑ ሰዓት ከፍትህ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ኃላፊነታቸው በተነሱት ዶ/ር ኃሺም መሐመድ ተጠርተው ተጠየቁ። ወ/ት ብርቱካን የሰጡት ምላሽ ለሚመለከተው አካል መተላለፉን መንግሥት አስታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...


ዝርዝር ዘገባ የታከለበት 




