ኮ/ል መንግሥቱን ጨምሮ ሃያ የደርግ ባለሥልጣናት የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው

  (ተጨማሪ ጥንቅር የታከለበት ዘገባ ስለሆነ ያንብቡት!!!)  

  • ይግባኛቸው ውድቅ ተደረገ
  • በሰበር ችሎት ይግባኝ ማለት ይችላሉ

Col. Mengistu Hailemariam

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. May 26, 2008)፦ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሲታይ የነበረው የደርግ ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት በሃያዎቹ ላይ ሞት በመፍረድ ዛሬ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ ከላከው ሪፖርት ለመረዳት ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቃለምልልስ ሰጡ

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. May 26, 2008)፦ ትናንት ማምሻውን የተደመጠው "የአደራ ቃል" ራዲዮ ከቀድሞው የቅንጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ትብርቱካን ሚደቅሳ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮችና ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ባለው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዙሪያ ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያልተሳካው የንዋይ ደበበ ኮንሰርት

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2000 ዓ.ም. May 25, 2008)፦ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም.፣ ንዋይ ደበበ በግዮን ሆቴል ኮንሰርት እንደሚያቀርብ ስሰማ በጉጉት ወደዚያው አመራሁ። በግዮን ከተደረጉ ኮንሰርቶች የቅርብ ትዝታዬ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ነበርና ከሱ ልምድ ወስጄ በጊዜ ወደ ሆቴሉ አመራሁ። አብሬ ልገባ የተቃጠርኩዋቸው ጉዋደኞቼም “ሰልፍ ይዘህ፣ ትኬት ቆርጠህ ጠብቀን” ሲሉ ከውሃ የወፈረች መልዕክታቸውን በስልኪቱ አስተላለፉልኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በወለጋ በጎሣ ግጭት ቢያንስ 93 ሰዎች ተገደሉ

ግጭቱ የተነሳው በቤንሻንጉሎች እና በኦሮሞዎች መሃከል ነው

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም. May 24, 2008)፦ ልክ የዛሬ ሣምንት ቅዳሜ ግንቦት ዘጠኝ ቀን 2000 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሞዎች መካከል በተነሳ ግጭት ዘጠና ሦስት ሰዎች እንደሞቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የንዋይ ደበበ ኮንሰርት ዛሬ ማምሻውን በግዮን ይጀመራል

ኮንሰርቱ እስከ መጪው ኅዳር ይዘልቃል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2000 ዓ.ም. May 24, 2008)፦ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ አርቲስት ንዋይ ደበበ በአዲስ አበባ በሚገኘው ግዮን ሆቴል “ዩኒቲ ሐውስ” በተባለው ቦታ የመጀመሪያውን ኮንሰርት እንደሚያሳይ ከአዲስ አበባ የደረሰን ሪፖርት ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዛሬ በአዲስ አበባ ድንገተኛ ፍተሻ ተካሄደ

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 15 ቀን 2000 ዓ.ም. May 23, 2008)፦ ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚያስረዳው በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ብዛት ያላቸው የፌደራል ፖሊሶች መንገደኞችንና መኪኖችን በማስቆም ከፍተኛ ፍተሻ በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቴዲ አፍሮ ላይ ዓቃቤ ሕግ ሦስት ምስክሮቹን ትናንት ፍ/ቤት አቀረበ

ሦስቱም ምስክሮች ፖሊሶች ናቸው

 

Teddy Afro

Ethiopia Zare (ኀሙስ ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም. May 22, 2008)፦ ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የነበረው ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሳሁን) ላይ ከሳሹ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቼ ካላቸው አራቱ ውስጥ ሦስቱ ግለሰቦች አቀርበው ነበር። የቀረቡት ሦስቱም የቀረቡት ምስክሮች ፖሊሶች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በታክሲ ፍንዳታው የሞቱት ስድስት ናቸው

• የአራተኛው አስከሬን በማግሥቱ በሼህ አላሙዲን መናፈሻ ውስጥ ተለቅሞ ተገኘ

• 5ኛውና 6ኛው አካላቸው ተቆራርጦ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ አርፈዋል

• አንዱ በትውልድ እስራኤላዊ በዜግነቱ አሜሪካዊ ነው

Ethiopia Zare (ኀሙስ ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም. May 22, 2008)፦ ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ወደ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ በአዲስ አበባ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጎን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ድርጅት በር ላይ በሚኒባስ ታክሲ ላይ በደረሰው ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ስድስት መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢ ገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሸምጋዮቹ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም. May 21, 2008)፦ ምርጫ 97ን ተከትሎ በርካቶች ወደ እስር ከተወረወሩ በኋላ፣ በተለይም የቅንጅትን ከፍተኛ አመራሮችና ከምርጫው ጋር በተያያዘ የታሰሩትን ሰዎች ያስፈቱት የሀገር ሽማግሌዎች ወደ አሜሪካ በያዝነው ሣምንት እንደሚሄዱ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...