ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቅዱስ ገብርኤልን በዓል በዲሲ አከበሩ

የመኖሪያቸውና ጽህፈት ቤታቸው ግንባታ እየተጠናቀቀ ነው!

የበአሉ እለት፡ በቤተመቅደስ ውስጥ መለስተኛ ረብሻ ተነስቶ ነበር!

Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም. January 2, 2011)፦ በውጭ ሀገር በስደት ላይ የሚገኘውና ህጋዊው ሲኖዶስ ብጹዕ ወቅዱስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ አቡነ መርቆሪዮስ መቀመጫቸውን በአሜሪካዋ መናገሻ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ እንደሚያደርጉ እና ጽህፈት ቤታቸውና የመኖሪያ ቤታቸው ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በደሴ ከተማ 11 ቤቶች ተቃጠሉ

ሕዝብ እና ፌደራል ፖሊስ ተፋጠዋል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. December 27, 2011)በደሴ ከተማ ልዩ ስሙ አራዳ ገበያ በመባል የሚታወቀው ቦታ 11 ቤቶች ተቃጥለው ነዋሪዎች በድጋሚ በእሳት የጋዩ ቤቶቻቸውን ለመስራት  ሲሞክሩ በስፍራው የደረሱ የፌደራል ፖሊሶች ቤቶቹ እንዳይሰሩ በመከልከላቸው ምክንያት  ህዝብና የፌደራል ፖሊስ መፋጠጣቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ጠቆመ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍርድ ቤት ድራማ በተደናገጡና በተምታቱ ምስክሮች ለቅሶ ተገባደደ፤ ዛሬም ይቀጥላል

ምንጭ፦ አዲስ ነገር

ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ፡- የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ላይ በኢቲቪ አኬልዳማ ዶኩመንተሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን በዋና ምስክርነት አቀረበ። ብዙዎቹ መስካሪዎች በጭንቀትና በመርበትበት ሲናገሩ፣ አንዳንዶቹም ሲያለቅሱ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮ/ል መንግስቱ “ትግላችን” መጽሐፍ በገበያ ላይ ይውላል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. December 17, 2011)፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ሰዓት በስደት ዚምባቡዌ የሚገኙት፤ በመጥፎነታቸው የሚታወቁት የኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ባለ ሶስት ቅጽ መጽሐፍ የመጀመሪያው ክፍል በሚቀጥለው ሳምንት በገበያ ላይ ሊውል ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ የፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ተጠናክሯል

የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በየቤታቸው ይፈተሻሉ

Ethiopia Zare (አርብ ህዳር 29 ቀን 2004 ዓ.ም. December 9, 2011) በመናገሻዋ አዲስ አበባ በየትላልቅ ፎቆችና ዋና ዋና መንገዶች ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ በመባል የሚታወቁት ተወርዋሪ የጥበቃ ኃይሎችና የደህንነት አባላት ሩጫ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ መታየታየቱ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦባንግ ሜቶ ኦታዋ ገባ፡ በኮንጎዎች የተቃውሞ ሰልፍ ላይም ተሳተፈ

“የኦታዋና ቶሮንቶ ኢትዮጵያዊያንን እንቅስቃሴ ያሳድጋል” ተብሎ ተስፋ ተደርጓል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ህዳር 28 ቀን 2004 ዓ.ም. December 8, 2011)፦ የጋራ ንቅናቄ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛው Solidarity Movement for New Ethiopia የተባለው የተባለው መቀመቻው በሰሜን አሜሪካ የሆነ የኢትዮጵያዊአን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መስራችና ስራ አስኪአጅ አቶ ኦባንግ ሜቶ፡ ቀድሞ ይኖርበት ከነበረው ሳስካቱን ከተማ ወደ ካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ በዚህ በያዝነው ሳምንት መዛወሩ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በካናዳ ዋና ከተማ፡ ኦታዋ፡ የኔሰው ገብሬ በሻማ ማብራት ስነስርአት ታሰበ

አያሌ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት ተገኝተው ነበር

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ህዳር 26 ቀን 2004 ዓ.ም. December 6, 2011)፦ ከማል አቡበከር ይባላል። የአገሩ ጉዳይ የሚያንገበግበው ጎልማሳ ነው። በእለቱ የቤቱን እቃ ለማጓጓዝ የጭነት መኪና ለስድስት ሰዓት ያህል ቢከራይም፡ የየኔሰው ገብሬ መታሰቢያ እንደሚደረግ ስነግረው፡ መኪናውን ከመንገድ ጥግ አቁሞ ወደ ካናዳ ፓርላማ ለመጓዝ ሰከንድም አልፈጀበትም። “አረ ትኬት እንዳይሰጡህ” ቢባልም “እንኩዋን ትኬት መስጠት፡ ጎትተውም ይውሰዱት ከፈለጉ” ብሎ ወደ ሻማ ማብራቱ አቀና። እሁድ፡ ዲሴምበር 4፡ 2011 ዓ.ም፡ ከሰኣት በኋላ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ የሚካሄደው የግብረሰዶማዊያን ስብሰባ ቁጣ ቀስቅሷል

የኃይማኖት አባቶች ድፍረት ይጎላቸዋል ተባለ

"ይህንን በህይወት በማየቴ እጅግ ስሜቴ ተነክቷል" ጋዜጠኛ ሰይፉ መኮነን

ተቃውሟቸው የታይታና ግብዝነት የሞላበት ነው” ተክለሚካኤል አበበ

Ethiopia Zare (አርብ ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም. December 2, 2011)፦ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ነገ ቅዳሜ፡ ዲሴምበር 3 በአፍሪካ የግብረ ሰዶማዊያን ቡድን አሰባሳቢነት በጤና ጉዳዮች ላይ በጁፒተር ሆቴል የሚካሄደው ስብሰባ በዚህ ሳምንት በህብረተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ከመሆኑም በላይ በተለይ የሀይማኖት አባቶች የወሰዱት አቋም ቀድሞም ቁርጠኝነት ያልነበረውና ወላዋይነት የሞላበት መሆኑ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሱዳን ኢትዮጵያዊውን የፖለቲካ ስደተኛ ለኢህአዴግ አሳልፋ ሰጠች

Ethiopia Zare ( እሁድ ኅዳር 17 ቀን 2004 ዓ.ም. November 27, 2011)፦ የሱዳን መንግስት በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ እስርና እንግልት እያደረሰ ነው በሚል እየተወነጀለ ባለበት በአሁኑ ወቅት አንዷለም አለማየሁ የተባለውን የኢህአዴግ ተቃዋሚ አሳልፎ ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሰጠ ከደረሰን ዜና መረዳት ተችሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ጦር በድጋሚ ወደ ሶማሊያ ሊዘምት ነው

ፕሬዝዳንቱ አልፈለጉምየሶማሊያ ባለስልጣን

ተጠቃሚው አል-ሻባብ ነውየፖለቲካ ተንታኞች

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. November 19, 2011)፦ የሶማሊያ አብዛኛውን ክልል የተቆጣጠረውና ከአልቃይዳ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አለው የሚባለውን አል-ሻባብን ለመመንጠር፤ የአፍሪካ ህብረት በድምሩ 10 ሺህ የሚገመት ጦር ለመላክ እየሞከረ ሲሆን የኢትዮጵያን ጦር ተሳትፎ በተመለከተ ግን ካሁኑ አወዛጋቢ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...