የክራር ንግሥቷ አስናቀች ወርቁ በ76 ዓመቷ አረፈች
የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ነገ በሥላሴ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል
Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 4 ቀን 2004 ዓ.ም. September 15, 2011)፦ ”የክራሯ ንግሥት” በመባል የምትታወቀው አንጋፋዋ የመድረክ ባለሙያ አስናቀች ወርቁ በ76 ዓመቷ ለረዥም ጊዜ በሕክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ ሕይወቷ አለፈ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ነገ በሥላሴ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል
Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 4 ቀን 2004 ዓ.ም. September 15, 2011)፦ ”የክራሯ ንግሥት” በመባል የምትታወቀው አንጋፋዋ የመድረክ ባለሙያ አስናቀች ወርቁ በ76 ዓመቷ ለረዥም ጊዜ በሕክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ ሕይወቷ አለፈ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የመድረክ አመራር አንዷለም አራጌና ሌሎች 3 አባላትም በማዕከላዊ ናቸው
Ethiopia Zare (ረቡዕ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. September 14, 2011)፦ በደፋርነቱና ለሀገሪቱ መጻኢ ዕድል ያለውን ዕይታ ነጻ የሆኑ ሃሳቦቹን በመግለጽ የሚታወቀው እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት በደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸው ተገለጸ።
ዳኛ ብርቱካን አዲሱን ዓመት በስዊድን ከኢትዮጵያውያን ጋር አሳለፉ
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 1 ቀን 2004 ዓ.ም. September 12, 2011)፦ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ከኢትዮጵያውያን ጋር አዲሱን ዓመት ለመቀበል በተዘጋጀ ልዩ ዝግጅት ላይ በመገኘት በስደት ላይ ለሚገኙና በሀገር ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞታቸውን ገለጹ። ዜጎችን ያስጎነበሰውን የየሀገራቸውን ሥርዓት ለሁልጊዜ እንደቀየሩት ህዝቦች ሁሉ፤ በአዲስ ተስፋ፣ በአዲስ ሃሳብ ለኢትዮጵያ በአንድነት የምንሠራበት ዘመን ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናገሩ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ድርጅት አዲስ አመራር ኮሚቴ መረጠ
Ethiopia Zare (አርብ መስከረም 1 ቀን 2004 ዓ.ም. September 12, 2011)፦ ላለፉት ሶስት አመታት በየአመቱ በተከታታይ ሲካሄድ የቆየው፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመከላከልና በማስጠበቅ ሲተጉ የኖሩ የጦር መኮንኖችንና ታጋዮች የሚሸልሙበት የጀግኖች ምሽት ዝግጅት እንደማይኖር አንዳንድ ውስጣዊ ምንጮች ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
በሽብርተኛ ክስ ውብሸት ጥላሁን፣ ርዮት አለሙ እና ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ክስ ተመስርቶባቸዋል
Ethiopia Zare (አርብ ጳጉሜን 4 ቀን 2003 ዓ.ም. September 9, 2011)፦ ታዋቂው የጥበብ ባለሙያና የቅንጅት ለአንድነትና ዲሞክራሲ አመራር አባል እንደነበር የሚታወቀው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኢህአዴግ መንግስት “ሽብርተኛ” ተብሎ ከተፈረጀው ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ግንኙነት አድርጓል በሚል ማእከላዊ እስር ቤት መግባቱ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
[ማሳሰቢያ፦ ቪዲዮውን ሕፃናት አይዩት!]
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. August 30, 2011)፦ የሊቢያው መሪ ልጅ የሆነው የሃኒባል ጋዳፊ ባለቤት ወ/ሮ ኤሊን በፈላ ውሃ ከአናትዋ ጀምሮ ፊትዋንና መላ ሰውነቷን ያቃጠለቻት የ30 ዓመቷን ኢትዮጵያዊት ወጣት ሸዋዬ ሞላ በትሪፖሊ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላት መሆኑን ሲኤንኤን ዘገበ። አደጋውን ያደረሱት አልጄሪያ ተሰድደዋል።
[ማሳሰቢያ፦ ለሕፃናት ያልተፈቀደ!]
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. August 30, 2011)፦ የሊቢያው መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ የሆነው ሃኒባል ጋዳፊ ባለቤት ወ/ሮ ኤሊን የ30 ወጣት ሸዋዬ ሞላ የተባለች ኢትዮጵያዊቷን የልጆችዋን ሞግዚት የፈላ ውሃ ከአናቷ ጀምራ መላ አከላቷ ላይ ደጋግማ በማፍሰስ እንዳቃጠለቻት ሲኤንኤን የተሰኘው ቴሌቭዥን አጋለጠ። የሙአመር ጋዳፊ ቤተሰቦች እንዲህ በመሰው ጭካኔና ግፍ በተሞላበት መንገድ ሰዎችን ላለፉት 42 ዓመታት ሲያሰቃዩ፣ ሲጨፈጭፉ፣ ሲገርፉ፣ ሲገድሉ፣ ... እንደነበር ይታወቃል። ሙሉውን የሲኤንኤን ዘገባ የማጫወቻ ቁልፉን በመጫን ይመልከቱ! [ዘገባውን ሕፃናት ሊያዩት አይገባም!]
Ethiopia Zare (አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2003 ዓ.ም August 26 2011) :- ባለፈው ግንቦት የተቋቋመውና መቀመጫው በቶሮንቶ የሆነው “አድባር የክርክር ማህበር” ሶስተኛውን የክርክር ዝግጅት በያዝነው ሳምንት፡ አርብ፡ ኦገስት 26 ከሰዓት በኋላ፡ ከ5 ሰዓት ጀምሮ፡ በሂሩት የሀበሻ ሬስቶራንት እንደሚያደርግ በላከው አጭር መግለጫ አስታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ስብሰባው በካሜራ እንዲቀረጽ ተፈቅዷል
“ለተቃዋሚ ሀይሎች ኅብረት ምስረታ ከግንቦት ሰባትና ሌሎች ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር እየሰራን ነው”
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2003 ዓ.ምAugust 16) የቀድሞ የሕወሀት መስራችና የነጻነት ታጋዩ ዲባቶ አረጋዊ በርሄ በመጪው ቅዳሜ፡ ኦገስት 20 በካናዳ ዋና ከተማ፡ ኦታዋ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ከኦታዋ የሚተላለፈው የኢትዮጵያ ሬድዮ ዘገበ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...