የዲያስፖራ ኢትዮጵያ ሰላዮችን እናጋልጥ!

EMF -- የኢትዮሜዲያ ድረ-ገጽ "Bad news for Meles Zenawi spies in the U.S." ብሎ ባሰፈረው ዜና የቨርጂኒያው መሃመድ አናስ ሱኢድ ለሶሪያ አንባገነን መንግሥት ሲሰልል ተይዞ መታሰሩን ገልጾ፤ ይህም በዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ካገኙ በኋላ ለአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ለሚሰልሉ የገዢው ፓርቲ አገልጋዮች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አስፍሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

እስረኞቹ ከአንድ ወር በኋላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አይተዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም. October 13, 2011)፦ በማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተወሰደባቸውና በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ሌሎች እስረኞች በድጋሚ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ተመልሰዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ በሶማሌ ላንድ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ስደተኞች እንዲታፈሱለት ጠየቀ

300 የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስደተኞች በሀርጌሳ ታስረዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. October 8, 2011)፦ የኢህአዴግ መንግስት በሱማሌ ላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች ታፍነው እንዲመለሱለት ትእዛዝ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት እስካሁን 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሰሳ ተይዘው በሀርጌሳ እስር ቤቶች ውስጥ የታጎሩ ሲሆን በቅርቡም ወደ አዲስ አበባ ይላካሉ ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአምባሣደር ዘውዴ ኃይለማርያም ሥርዓተ ቀብር በስቶክሆልም ተፈጸመ

Ambassador Zewde HaileMariamEthiopia Zare (ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2004 ዓ.ም. September 26, 2011)፦ አምባሣደር ዘውዴ ኃይለማርያም በደረሰባቸው ሕመም ስቶክሆልም በሚገኘው ካሮሊንስካ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ነኀሴ ፴ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. በ፹ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሥርዓተ ቀብራቸውም ረቡዕ መስከረም ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ሶልና በሚገኘው በኖራ ግራቭኒንግስ ፕላትስ ተፈጽሟል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች መግለጫ አወጡ

እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬና ርዕዮት ዓለሙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2004 ዓ.ም. September 26, 2011)፦ በነፃ ፕሬስ ላይ በሚደረገው ጫና፣ እስርና እንግልት ምክንያት በስደት ላይ የሚገኙ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች በ’ሽብርተኝነት’ ስም በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙ ላይ የተፈጸመውን እስር አወገዙ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

”በሽብርተኝነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!” መድረክ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 13 ቀን 2004 ዓ.ም. September 24, 2011)፦ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ፣ የኦፌዴን ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የኦህኮ የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳ፣ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ናትናኤል መኮንንና አቶ አሳምነው ብርሀኑ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፣ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ፣ ጋዜጠኛ ስለሽ ሐጎስ እንዲሁም አርቲስት ደበበ እሸቱ የአንባገነናዊው ሥርዓት ጅምላ እስራት ሰለባ ከሆኑት ጥቂቶቹ መሆናቸውን መድረክ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው መግለጫ ገለፀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የፖለቲካ አስረኞቹ በአስቸኳይ ይፈቱ!” በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማኅበር

AEUP support in North AmericaEthiopia Zare (ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም. September 23, 2011)፦ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ “ከሽብርተኞች ጋር ንክኪ አላቸው” የሚል መሰረተ ቢስ ክስ እየመሰረተ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራር አባላትን፣ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችንና አርቲስቶችን ወደ እስር ማጎሩን አስመልክቶ በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጪ ማኅበር ትናንት ባወጣው መግለጫ እስረኞቹ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የታሰሩት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አባላቶቼ አይሉም” ግንቦት 7

Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 11 ቀን 2004 ዓ.ም. September 22, 2011)፦ ባለፈው መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አንዷለም አራጌንና ሌሎች ሦስት የፓርቲውን የምክር ቤት አባላትና እውቁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት ኢህአዴግ ያሠራቸው ግለሰቦች ”ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም” በማለት ግንቦት ሰባት መግለጫ አወጣ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሕአዴግ መንግስት 52 ቢሊየን ባለ100 እና 50 ብር ኖቶች ሊያሳትም ነው

ግሽበቱን ያባብሰዋለረ ተብሎ ተሰግቷል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 2004 ዓ.ም. September 17, 2011)፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ 52 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አዳዲስ የመቶ እና የሃምሣ ብር ኖቶችን ሊያሳትም መዘጋጀቱ ተሰማ። በሀገሪቱ ታሪክ ይህንን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ታትሞ የማያውቅ ሲሆን ለማሳተም ብቻ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ ተገምቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...