የብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ የቀብር ስነ ስርአት በሲያትል ይፈጸማል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም August 3, 2011):- በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የብጹእ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ ክቡር ሥጋ የሚያርፍበት ቦታ ለማዘጋጀት ባወጣው እቅድ መሰረት በስማቸው በተሰየመውና ቴክሳስ - ሂውስተን በተመሰረተው ገዳም ለማሳረፍ ያደረጋቸው ሙከራዎች ጊዜ በመውሰዱ ለጊዜው ብጹእነታቸው ብርታት ከእዳ ነጻ አድርገው በሲያትል ከተማ ባቋቋሙት መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል የቀብር ስነስርአታቸው እንዲፈጸም ወሰነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኦታዋው ግልጽ ህዝባዊ ስብሰባ፡ በስውር ተጠናቀቀ

የብሄር ድርጅቶችን፡ አቅርቦ መያዝ እንጂ፡ ሙሉ በሙሉ ማግለሉ አግባብ አይደለም እኔ

የብሄር ድርጅቶችን እንደውም መድረክ በመስጠት ማጠናከር ሳይሆን ማጥፋት ነው አንድ ተሳታፊ 

የኢትዮጵያን አንድነት የማይቀበሉ የብሄር ድርጅቶችን እንደውም ወደፊት እንደወያኔ የምንዋጋቸው ናቸው ዶ/ር ኤርሚያስ ዓለሙ 


ልዩ ዘገባ - ልጅ ተክሌ (ኦታዋ-ካናዳ)

 

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2003 ዓ.ም. July 14, 2011):- እሁድ ጁላይ 24፡ 2011 ዓ.ም.፡ መቀመጫው በኦታዋ የሆነው፡ “የኢትዮጵያ ካናዳዊያን መድረክ ለዴሞክራሲ” (በእንግሊዘኛው “Ethio-Canadians Forum for Democracy”፡ ከፖለቲካ እስረኞች አንድነት ማህበር፡ ከኢህአፓና፡ ከዓለም-አቀፋዊው የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር ምስረታ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በመተባበር፡ በኦታዋ ያዘጋጀው ስብሰባ የተለያዩ፡ ሀሳቦች ተንሸራሽረውበት ተጠናቀቀ። ዝግጅቱ ግን እንዳይቀረጽ መከልከሉ ጥቂቶችን አስቆጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምስራቅ ኢትዮጵያ አስከፊ ረሃብ አሳሳቢ ሆኗል

ሊያነቡት የሚገባ ልዩ ዘገባ - ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. July 14, 2011):- ህጻናት ረሃብ ሳል እአሰሙ ነው። እናቶች የልጆቻቸውን አሰቃቂ ሞት በአይናቸው ለማየት ተገደዋል። እርፍ ጨብጠው መሬቱን እገመሰ ዘርቶ፣ አችዶና ሰብስቦ ለሌላው ይተርፍ የነበረው ገበሬ ተስፋ የቆረጡ አይኖቹ እንባቸው ደርቋል። ለሰው ልጆች ተስፋ የነበሩት ዕጸዋት ጠውልገዋል።ከብቶች በሜዳው ላይ ወድቀዋል። የተስፋ ጭላንጭል ተዳፍኖ የሞት ደመና በሚሊየኖች የሚቆሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አንዣቧ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመጨረሻም ብርቱካንም ተናገረች፤ ያምቡሌም ተዘፈነ፡ ወጣቶቹም ሮጡ፡ ኢትዮጵያም ተከበረች፡ ፌስቲቫላችንም ተሳካ፡

(የግል ዘገባ - በልጅ ተክሌ)

ብዙዎች አስቦክተውን፡ ብዙዎችም አስጠንቅቀውን ነበር

 አንዳንዶቹ፡ “አይ አይሳካላችሁም፡ እንደው ነው የምትደክሙት” ብለው አስፈራርተውን ነበር። ገሚሶቹም፡ “ባዶ ሜዳ ታቅፋችሁ ትቀራላችሁ” ብለው ፈልፍለውብን ነበር። የተቀሩት ግን “በርቱ፡ እኛም እንመጣለን” አሉን። እነሆ ገሚሱን ታቅፈን፡ ገሚሱንም አዝለን ወደፊት ገሰገስን፤ የዛሬ አስር ወር በሀሳብ ደረጃ፡ የዛሬ ስድስት ወር በህግ ደረጃ፡ የዛሬ ሁለት ወር ወዲህ ደግሞ በተጨባች የተያዘውን ፌስቲቫል አርብ ስንከፍት ግን፡ ገና ከመክፈቻው ሰዓት አስቀድሞ የመክፈቻው አዳራሽ ላይ የተጠራቀሙት ሰዎች ቁጥር ተስፋ ፈንጣቂ ነበር።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ዛሬም ስለ ሀገሬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አጠንክሬ ህልም አልማለሁ” ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

          ‘ኢትዮጵያ የነጻነት ሀገር አይደለችም፤ የፍትህ አገር አይደለችም’

Ethiopia Zare ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2003 ዓ.ም. July 5, 2011:- ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ ባዘጋጀው ፌስቲቫል በህዝብ ፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር አደረገች። የቪድዮ መልእክታ ተሰራጭቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ሁለተኛ ቀን ባስደሳች ሁኔታ አለፈ

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2011 .. July 3 , 2011):- አርብ፡ ጁላይ 1 ቀን በዋሽንግተን ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አመታዊ ፌስቲቫል  በሁለተኛው ቀን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሎ ውሏል። ዛሬ እሁድ ፍጻሜ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ልትናገር ነው

Ethiopia Zare (አርብ ሰኔ 24 ቀን 2011 .. July 1 , 2011):-  በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ አዘጋጅነት በሚካሄደው ታላቅ ፌስቲቫል ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ህዝብ ፊት ቀርባ ንግግር ልታደርግ መሆኑን ባልደረባችን ተክለሚካኤል አበበ ከስፍራው አስታወቀ። ዝርዝሩን እንደሚከተለው አቅርቦታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ "ለቡኤርቱ" የተባለ ሰፈር 1027 ቤቶች ፈረሱ

                    አንድ ነዋሪ ድልድይ ውስጥ ራሱን ወርውሯል ሁለቱ በጅብ ተበልተዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. June 30, 2011):-  ለቡኤርቱ በተባለ ሰፈር ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ የተገነቡ 1027 ቤቶች መፍረሳቸውንና ከቤቶቹ ባለቤቶች አራቱ ህይወታቸውን ማጥፋታቸውን የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አድባር የክርክር ክበብ የመጀመሪያውን መድረክ አዘጋጀ

ባህላችን በፖለቲካችን ያለው ገጽታ አዎንታዊ ወይንስ አሉታዊ?

Ethiopia Zare (አርብ ሰኔ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. June 24, 2011):- በካናዳዋ ዋናየንግድ ከተማ ቶሮንቶ የተቋቋመው አድባር የክርክር ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያዘጋጀው መድረክ ጋዜጠኛና የህግ ተማሪ የሆነው ዳንኤል ጥላሁንና የሲቪል ኢንጂኒዬሪንግ ምሩቅ የሆነው ወጣት ኪሩቤል ፍሬው በሚያካሂዱት ክርክር እንደሚጀመር ተገለጸ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...