የኢህአዴግ መንግሥት አቶ ስዩም መስፍንን ወደ ቻይና ላከ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 9 ቀን 2003 ዓ.ም. November 18, 2010)፦ ’መተካካት’ በሚል መርኅ የሥልጣን ለውጥ እንደሚያደርግና በአዳዲስና ወጣት ተሿሚዎች እንደሚተካ ቃል የገባው የኢህአዴግ መንግሥት፤ የቀድሞ ቱባ ቱባ ባለሥልጣናቱን በቋሚ ወይንም በባለሙሉ ሥልጣን አምባሣደርነት መሾሙን ካሳወቀ በኋላ፤ ትናንት አቶ ስዩም መስፍንን ወደ ቤጂንግ እንደሚልክ ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ሩጫ መመለሱን አበሰረ

Haile GebreselassieEthiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. November 15, 2010)፦ በረዥም ርቀት ውድድሮች ተደጋጋሚ የክብረ ወሰኖች ባለቤት የሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴ በድጋሚ ወደ ሩጫ እንደሚመለስ በክብር እንግድነት የተገኘበት ነቀምት ከተማ ህዝብ ፊት በመቅረብ ይፋ አደረገ። ከኒው ዮርኩ ውድድር ነኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣይ ለሚደረገው የለንደኑ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚቀጥልም አብስሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የሰማዕታት ቀን ተከበረ

Judge Woldemichael Meshesha, ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ”ያወጣው አካል ያላከበረው ሕግ እንዳልተፃፈ ይቆጠራል” ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 4 ቀን 2003 ዓ.ም. November 13, 2010)፦ ከስዊድን በዕለተ እሁድ ከጠዋቱ አራት ሰዓት (10፡00 ሰዓት) ጀምሮ የሚተላለፈው የኢትዮጵያ ድምፅ ሬድዮ የዕለቱን ዝግጅት የጀመረው ’’አይ ሽብሬ” በሚለው ለሰማዕታት ቀን መታሰቢያ በተዘጋጀው ግጥም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውሮፓ ህብረት የምርጫ 2002 ዓ.ም. ዝርዝር ሪፖርት አቀረበ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. November 9, 2010)፦ ከአምስት ወራቶች በፊት በኢትዮጵያ የተካሄደውንና በወያኔ/ኢህአዴግ 99.6% አሸናፊነት እንደተጠናቀቀ የተገለጸውን ‘ምርጫ’ 2003 በሚመለከት የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን ዝርዝር ሪፖርቱን አወጣ። ምርጫው ግልጽና ለሁሉም ተቃዋሚዎች የተመቻቸ የመጫዎቻ ሜዳ ማዘጋጀት ያለመቻል ጉድለት ነበረው ሲልም መግለጫው አብራርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኃይሌ ገብረሥላሴ ጡረታ መውጣት አስተያየቶች እየጎረፉ ነው

Haile Gebrselassie of Ethiopia crossed the finish line at the Berlin Marathon on Sunday Sep. 28, 2008, setting a new world record.

የኒው ዮርኩን ማራቶን አትሌት ገብሬ ገብረማሪያም አሸነፈ

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. November 8, 2010)፦ አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ትላንትና በተካሄደው የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ላይ በተሰማው ሕመም ምክንያት አቋርጦ ከወጣ በኋላ በሰጠው መግለጫ ራሱን ከአትሌቲክስ ጎራ ጡረታ እንደሚያወጣ ይፋ አደረገ። በአስደንጋጩ የአትሌት ኃይሌ ውሳኔ የተለያዩ አስተያየቶች እየጎረፉ መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ሂሩት በቀለ ሞተች” የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑ ተረጋገጠ

Hirut Bekele ሂሩት በቀለ ለአዲስ ድምፅ ራዲዮ ቃለምልልስ ሰጠች

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም. November 4, 2010) ፦ ”ታዋቂና ተወዳጅዋ አርቲስት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች” ሲል በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው ”የሀገር ፍቅር ራዲዮ” ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. ያሠራጨውን ዘገባ ተከትሎ ወሬው ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ተዳርሶ ከፍተኛ ኀዘን በኢትዮጵያውን ዘንድ ተፈጥሮ ነበር። ዜናው ሐሰት መሆኑንና አርቲስቷ በሕይወት እንደምትገኝ ከአዲስ ድምፅ ራዲዮ ጋር ቃለምልልስ በማድረጓ ተረጋግጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአክብሮትና የሰማዕታት መታሰቢያ ቀናት እንደሚከበሩ ተገለጸ

Judge Woldemichael Meshesha, ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ማትያስ ከተማ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. November 3, 2010)፦ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 27 ቀን 2003 ዓ.ም. (ኖቬምበር 6 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን መፈታት አስመልክቶ ”የአክብሮት ቀን” ብለው የሚያከብሩ ሲሆን፣ እሁድ ጥቅምት 28ን (ኖቬምበር 7ን) ደግሞ ምርጫ 97ን ተከትሎ ለተጨፈጨፉት የሰማዕታት ቀን መታሰቢያ ሊያከብሩ ነው። በዝግጅቱ ላይ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ይገኛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲኖዶሱ የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ ወሰነ

በአንድ ራስ ሁለት ምላስ - አቡነ ጳውሎስ

Abune Paulos, አቡነ ጳውሎስ”አልተሳሳትኩም፣ ሐውልት ማሠራት በእኔ አልተጀመረም” አቡነ ጳውሎስ

”ሐውልት መሠራቱን አላውቅም፤ ሐውልቱ ሲገለጥ ነው ያየሁት” አቡነ ጳውሎስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. October 26, 2010)፦ አዲስ አበባ ጉባዔ ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ከብዙ የአባቶች ውትወታ በኋላ ስለ ሐውልታቸው ጉዳይ ዛሬ ምላሽ የሰጡት አባ ጳውሎስ፤ ሁለት የተጻረሩ ሃሳቦችን በማቅረብ መደናገር እንዲፈጠር ቢያደርጉም፤ ሲኖዶሱ ሐውልታቸው እንዲፈርስና ፖስተሮቹም ከተሰቀሉበት እንዲነሱ ወሰነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...