የኢትዮጵያው ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባዔ ውጥረት ላይ ነው

አቡነ ጳውሎስ ስለሐውልታቸውና ፖስተሮች ጉዳይ ነገ ምላሽ እሰጣለሁ አሉ

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2003 ዓ.ም. October 25, 2010)፦ ባለፈው ሣምንት ዓርብ በአዲስ አበባ የተጀመረውና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባዔ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኗ ችግሮች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ በተለይ በአቡነ ሳሙኤልና በአቡነ ጳውሎስ ሐውልት ማሰራት ጉዳይ ላይ ሰፊ ክርክሮች እየተደረጉ መሆኑ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እንድትፈታ ለተሟገቱ ካናዳዊያን የምስጋና ዝግጅት ተሰናዳ

በተለይ ክቡር ሚስተር ፒተር ጁሊያንና ፓርቲያቸው አብዩን ሚና ተጫውተዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 6 ቀን 2003 ዓ.ም. October 16, 2010)፦ ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር እንድትፈታ የካናዳን ፓርላማ በመወትወት የሚታወቁትና የበርናቢ ኒውዌስት ሚኒስትር የኤን. ዲ. ፒ. ፓርቲ የፓርላማ ተመራጭ የሆኑት ክቡር ሚስተር ፒተር ጁሊያንንና አጋሮቻቸውን የሚያከብርና ለብርቱካን መፈታት ያደረጉትን አስተዋጽኦ የሚያደንቅ የምስጋና ስነስርአት በቫንኩቨር ነዋሪዎች መዘጋጀቱ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ተፈቱ

Hale & W/t Birtukan

Ethiopia Zare (ረቡዕ መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም. October 6, 2010)፦ ላለፉት 647 ቀናት በቃሊቲ እስር ቤት ታስረው የነበሩት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም. (ኦክቶበር 6 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አምስት ሰዓት አካባቢ መፈታታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ረቡዕ ይፈታሉ

ከ647 ቀናት እስር በኋላ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ይቀላቀላሉ

W/t Birutkan MidekssaEthiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም. October 5, 2010)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ነገ ጠዋት ረቡዕ መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም. (ኦክቶበር 6 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) እንደሚፈቱ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለፁ። ለመፈታቱ ምክንያት የሽማግሌዎቹ ቡድን እጅ እንዳለበት ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠ/ሚ መለስ ሚኒስትሮቻቸውን አጸደቁ

አቶ ስዩም መስፍን በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተተክተዋል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም. October 5, 2010)፦ በ2002 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ መሰረት በብቸኛው ፓርቲ ኢህአዴግ ለመጭው አምስት ዓመታት የምትመራው ኢትዮጵያ ከትላንት ሰኞ ጀምሮ በተካሄደ የፓርላማ ተመራጮች ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አፈ ጉባዔ፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች የካቢኔ አባላትን አጸደቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር አሊያንስ አባል ሆነ

Mr. Jaan AlbrechtAto Girma WakeEthiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 20 ቀን 2003 ዓ.ም. September 30, 2010)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ”ስታር አሊያንስ” የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የአየር መንገዶች ሕብረት በሚቀጥሉት 12 ወራት ለመቀላቀል ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ተፈራረመ። አየር መንገዱ ከግብፅ እና ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ሕብረቱን ሲቀላቀል ሦስተኛው የአፍሪካ አየር መንገድ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጸደንያ ማሪያም ንግስ በቫንኩቨር ደምቆ ተከበረ

የጸደንያ ማሪያም ንግስ በቫንኩቨር ከሲያትል፣ ፖርትላንድ ካልጋሪና አሪዞና ምእመናን ተሰባስበው ነበር

በየአመቱ የሚከበረው የጸደንያ ማሪያም ንግስ አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ ዩሀንስ፣ አቡነ ሚካኤል (ከካልጋሪ)፣ ሁለቱ አባ ገ/ስላሴዎችና የቫንኩቨር ቅድስት ድንግል ማሪያም ደብር አባት መልአከ ጸሃይ አፍወርቅና አምስት መቶ የሚጠጉ ምእመናን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች በአደጋ ውስጥ ናቸው ተባለ

Ato Belachew Chekeneታምሩ ገዳ (ከለንደን)

ኢትዮጵያን በዓለም በታሪክ እና በቅርስ ባለቤትነት ተጠቃሽ ከሆኑት ጥቂት ሀገሮች መካከል አንዷ እንድትሆን ያደረጓት ታሪካዊ እና ኃይማኖታዊ ቅርሶቿ እጅግ አስጊ በሆነ የመጥፋት አዝማሚያ ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቫንኩቨር በመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን የበጋ ፌስቲቫል ደምቃ ዋለች

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ካናዳዊያንና አሜሪካዊያን ተገኝተው ነበር

“ብርቱካን መፈታት አለባት” የካናዳ ፓርላማ ተመራጭ ሚስተር ፒተር ጁሊያን

በቫንኩቨር ካናዳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ የክረምት ፌስቲቫል ከአሁን ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በፖለቲካ በሀይማኖትና በተለያዩ የማህበራዊ ችግሮች ምክንያት ተራርቆ የነበረው ነዋሪ በሙሉ በአንድ ላይ በመሰባሰብ በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...