የመለስ መንግስት በኦብነግ እንቅስቃሴ እንደተሸበረ ዊኪሊክስ አጋለጠ
ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የሽብር ጥቃት እንደሚያሰጋ ተገለጸ
አውስትራሊያ ዜጎቿን አስጠንቅቃለች
Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2003 ዓ.ም. January 26, 2011)፦ በቅርቡ የሚከፈተውን የአፍሪካ አንድነት ጉባኤ ተከትሎ የሽብር ጥቃት በአዲስ አበባ ሊደርስ እንደሚችል ታማኝ መረጃዎችን እንደሰበሰበች አውስትራሊያ አስታወቀች። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ የኤርትራ ሸብርተኞችን ያዝኩ አለች
Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 16 ቀን 2003 ዓ.ም. January 24, 2011)፦ የአፋር ክልልን አቋርጠው በመግባት በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ ከሻእቢያ የተላኩ ስልጡን ሽብርተኞች መያዛቸው ተገለጸ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች ኮሚቴ ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ
የካናዳ ባለስልጣናትና ኢትዮጵያዊ ምሁራን ንግግር ያደርጋሉ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 2 ቀን 2003 ዓ.ም. January 10, 2011)፦ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፖእአኮ) በካናዳዋ መናገሻ ኦታዋ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ከህዝብ ጋር ለመወያየት የካናዳ ፓርላማ ተወካይ ሚስተር ፖል ዲዋርንና የፒስ ቢልድ ዳይሬክተር ሚስተር ዴቪድ ሎረድን ጨምሮ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ፕሮፌሰሮችን በመጋበዝ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ ተገለጸ።አርቲስት ሔለን በርሔ ተመልካቹን አሸማቀቀች

- የብአዴን ዝግጅት ላይም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟት ነበር
- ነዋይ ደበበም አልተሳካለትም
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ ቀን 2003 ዓ.ም. January 4, 2010)፦ ባሳለፍነው አርብ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ በሚገኘው ሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በቅርቡ በአዲሱ የሙዚቃ አልበሟ ተደማጭነትን ያገኘችው አርቲስት ሔለን በርሔ እና አርቲስት ነዋይ ደበበ ተመልካቹን አሸማቀቁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አንጋፋው የእግር ኳስ ሰው መንግሥቱ ወርቁ በ70 አመቱ አረፈ
በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ግምባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነውና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋችነት እስከ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣንነት ስኬታማ ታሪኮችን ያስመዘገበው ታላቁ የእግር ኳስ ሰው መንግሥቱ ወርቁ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ታወቀ።
ከ97 ምርጫ በኋላ የት እንደደረሱ ያልታወቁ ዜጎች መኖራቸውን ኢሰመጉ ገለጸ
Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. December 9, 2010)፦ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ከረጀረም ጊዜ ቆይታ በኋላ የመብቶች ጥሰትን የሚያሳየውን 34ኛ መግለጫ ይፋ አደረገ። ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ የደረሱበት ያልታወቁ ዜጎች መኖራቸውን አትቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በስዊድን ’’እውነትም እኛ …” ተመረቀ
ግምገማና ውይይት ተደረገ

Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 27 ቀን 2003 ዓ.ም. December 6, 2010)፦ በጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ ተገጥሞ በራሳቸው አንባቢነትና በአቶ ክብረት መኮንን የምስልና ድምፅ ቅንብር የተደረገለት ”እውነትም እኛ …” የተባለ ሃያ አምስት ግጥሞች የያዘ ዲቪዲ የግጥም መድብል ቅዳሜ ኅዳር 18 (ኖቬምበር 27) ቀን በስቶክሆልም ከተማ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ተመረቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ በኤርትራ ፀጥታ ሀይሎች ታፍነው የደረሱበት አልታወቀም
በኤርትራ ያሉ የኢትዮጵያ ታጋዮች ስጋት ላይ ናቸው
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 25 ቀን 2003 ዓ.ም. December 4, 2010)፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባልደረባና ከጥቂት አመታት በፊት የአርበኞች ግንባር መስራችና ምክትል ሊቀመንበር፡ የነበረው ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ከኦክቶበር 25 ቀን ጀምሮ በአስመራ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ተወስደው መታሰራቸውንና እስካሁንም የደረሱበት እንዳልታወቀ በአስመራ የሚገኙ ምንጮቻችን ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭቱን እንደገና ጀመረ
Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም. December 2, 2010)፦ በምህጻረ ቃል ኢሳት (እሳት) በመባል የሚታወቀውና ዋና ቢሮውን በምድረ ሆላንድ ያደረገው የቴሌቪዥን አገልግሎት የቀጥታ ስርጭቱን ዛሬ ማለዳ ላይ በሙከራ መጀመሩን ይፋ አደረገ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...


