የ”ኢሳት” ቶምቦላ ወጣ፤ አሜሪካኖች ከፍተኛውን እጣ ወስደዋል

ካናዳዎችና አውሮፓዎችም ከእጣው ተጋርተዋል

ከጁላይ 29 እስከ ጁላይ 31 በአምስተርዳም በተካሄደው 8ኛው የኢትዮጵያዊያን አውሮፓውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ እንዲወጣ ታስቦ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (በምህጻረ ቃሉኢሳት”) መርጃ የተዘጋጀ ቶምቦላ ቅዳሜ ጁላይ 31 ቀን ከምሽቱ 8 ሰዓት አካባቢ አያሌ የኢሳት ደጋፊዎችና ጥቂት ተቃዋሚዎች በተገኙበት ወጣ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሌ/ኰ መንግሥቱ ኃይለማሪያም መጽሐፍ በኦፊሴል ነገ ገበያ ላይ ይውላል

L.Colonel Mengistu H.Mariamበዛሬው ዕለት ገበያ ላይ የዋለው ሁለት ሺህ ቅጂ በአንድ ሰዓት ውስጥ አለቀ

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 16 ቀን 2002 ዓ.ም. July 23, 2010)፦ በጋዜጠኛና ፀሐፊ ገነት አየለ የተዘጋጀው ”የሌተና ኰሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትዝታዎች (ቁጥር 2)” መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. (ጁላይ 24 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በኦፊሴል ገበያ ላይ ይውላል። ዛሬ ማምሻውን በጥቂቱ ለሽያጭ የቀረበው ሁለት ሺህ ቅጂ በአንድ ሰዓት ውስጥ ተሸጦ ማለቁን ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ሪፖርተር ዘግቧል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በዩጋንዳ-ካምፓላ ሁለት ፈንጂዎች ፈንድተው ከ64 በላይ ሰዎች ሞቱ

አንዱ ፈንጂ በኢትዮጵያዊያን ሬስቶራንት ውስጥ ፈንድቷል

Ethiopia Zare (እሁድ ሐምሌ 4 ቀን 2002 ዓ.ም. July 11, 2010)፦ በዩጋናዳዋ መናገሻ ካምፓላ ራግቢ ክለብ በተባለ ቦታና የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድርን ለመከታተል በአንድ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ውስጥ በተሰባሰቡ ሰዎች መሀል በፈነዱ ሁለት ፈንጂዎች ምክንያት በርካታ ኢትዮጵያኖችን ጨምሮ 64 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢሳት ሥርጭት የተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2002 ዓ.ም. July 06, 2010)፦ በጥቂት ሀገር ወዳዶች የጋራ ጥረትና ስብስብ ተቋቁሞ በኢትዮጵያና በሌሎች የዓለም ክፍሎች መሠራጨት የጀመረውን የኢትዮጵያ ሳይተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመርዳት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም ከተማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊያን በቶሮንቶ መለስን ተቃውመው ለመሰለፍ እየተሰናዱ ነው

ከዋሽንግተን ዲሲና ከቫንኩቨር ድረስ ኢትዮጵያዊያን እየገቡ ነው

ተክለሚካኤል አበበ-ከቶሮንቶ

እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠርኸ ከጁን 26 እስከ ጁን 27 በሚካሄደው የጂ 20 ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀውን አቶ መለስ ዜናዊና ተከታዮቹን ለመቃወም ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ከሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች አያሌ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቶሮንቶ ይገባሉ ብለው እንደሚጠብቁ አዘጋጆቹ ገለጹ።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሁለት ሺህ በላይ ተፈናቃይ ነዋሪዎች ሃያ እና አስር ሺህ ብር ተጠየቁ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2002 ዓ.ም. June 21, 2010)፦ በአዲስ አበባ ከአራት ኪሎ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ያሉ ቤቶች እንዲፈርሱ ተወስኖ፤ መሬቱ ለግል ባለሀብቶች መሸጡ ታወቀ። ተፈናቃዮቹ ከአቅማቸው በላይ ገንዘብ ከፍለው ኮንደሚንየም ቤቶች ውስጥ እንዲገቡ ተጠየቁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዋሽንግተን ዲሲው ሠልፍ የተሳካ እንደነበር ተገለፀ

March for freedom, Washington DC June14, 2010Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 10 ቀን 2002 ዓ.ም. June 17, 2010) ”ማርች ፎር ፍሪደም” በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ በኋይት ሐውስ እና በአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በጠራው ሠልፍ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው፤ የ2002ቱን ምርጫ ኢህአዲግ ማጭበርበሩን በመቃወም የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሚከተለውን ፖሊሲ እንዲቀይር ጠየቁ። ሠለፉ የተሳካ እንደነበር አዘጋጆቹ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለፁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቦሌ አየር ማረፊያ በሁለት ተጠርጣሪዎች ምክንያት በረራ እንዲዘገይ ተደረገ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. June 16, 2010) ባለፈው ሣምንት ማክሰኞ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ወደ ቴልሰቪቭ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ35 ላይ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል እንዲዘገይ ተደረገ። ይህም የሆነው በደህንነት ሰዎች የተጠረጠሩ ሁለት ተሳፋሪዎችን ተጨማሪ ፍተሻ ሲደረግላቸው መሆኑ ታወቀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለዓለም ዋንጫ ደ.አፍሪካ ለመሄድ 50 ሺህ ብር የከፈሉ ታገዱ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 9 ቀን 2002 ዓ.ም. June 16, 2010) በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን የ19ኛውን የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ለማየት ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ 50 ሺህ ብር የከፈሉ 550 ሰዎች ፈቃድ ተከለከሉ። ያስያዙት ገንዘብ አልተመለሰላቸውም። ሙሉውን አስነብበኝ ...