በቫንኩቨር ከካናዳው የፓርላማ ተመራጭ ጋር ህዝባዊ ስብሰባ ይካሄዳል

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የካናዳ መግቢያ (ቪዛ) እንዳይሰጣቸው ከፍተኛ ዘመቻ ተጀምሯል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 2 ቀን 2002 ዓ.ም. April 10, 2010)፦ በካናዳ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩባት የኒው ዌስት ሚኒስትርና በርናቢ አካባቢ የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ፒተር ጁሊያን ወ/ት ብርቱካንን ለማስፈታት በሚደረገው ጥረት ዙሪያና ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከኢትዮጵያውያኖችና ካናዳውያን ጋር ለመምከር ስብሰባ ጠሩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ ዕጩዎቼ እጅና እግራቸው ተሰብሮ የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል አለ

Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም. April 9, 2010)፦ መድረክ “በመንግሥትና በመንግሥቱ መገናኛ ብዙኀን የሚሰራጩ ገደብ የለሽ ስድቦች፣ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች፤ ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆኑና የሥነ ምግባር ደንቡን የሚፃረሩ በመሆናቸው በአስቸኳይ ይቁሙልኝ” ሲል መግለጫ አወጣ። በዕጩዎቼና በአባላቶቼ ላይ ደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድርጊቶች ይፋ አድርጓል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር አውደጥናት በዋሽንግተን ዲሲ

ከ30 በላይ አንጋፋና ወጣት ምሁራን ይሳተፉበታል

Ethiopia Zare (ሐሙስ መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም. April 8, 2010)፦ “ኢትዮጵያ ከየት ወዴት?” በሚል ርዕስ ዋና የመወያያ አጀንዳውን ሠላም፣ ፀጥታ፣ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳዳርን ያደረገ በርካታ ኢትዮያዊያንና የውጭ ሀገር ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፋቸውን የሚያቀርቡበት አውደ ጥናት ሊካሄድ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ምንጮቻችን ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ በውስጥና በውጭ ሀገር ከህዝብ ጋር ውይይቱን ሊቀጥል ነው

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2002 ዓ.ም. April 7, 2010)፦ የስምንት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው መድረክ፤ በመናገሻዋ አዲስ አበባ ከሚያደርጋቸው ህዝባዊ ውይይቶች በተጨማሪ ቅዳሜ እና እሁድ ሚያዝያ 2 እና 3 ቀን 2002 ዓ.ም. በኢሊባቡር፣ መቱና በምዕራብ ሸዋ ወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ ገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለወ/ሮ አረጋሽ አዳነ አሥራ አራት ሺህ ብር ተሰበሰበ

W/ro Aregash Adane ወ/ሮ አረጋሽ አዳነEthiopia Zare (እሁድ መጋቢት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. April 4, 2010)፦ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና በአሁኑ ሰዓት ዓረና-መድረክን በመወከል አቶ መለስ ዜናዊን በአድዋ በመፎካከር ለመጣል ቆርጠው ለተነሱት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ በቫንኩቨርና አካባቢዋ ነዋሪዎች የተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰብ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አዘጋጆቹ ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በፋሲካ በዓል የገበያው ዋጋ ንረት ታይቷል ተባለ

ዶሮ 80 ብር፣ ፍየል እስከ 2250 ብር፣ እንቁላል 2 ብር ተሽጧል

Ethiopia Zare (እሁድ መጋቢት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. April 4, 2010)፦ በዓለ ትንሣዔ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር እንደመሆኑ እንደባለፉት በዓላት ሁሉ ዘንድሮም የገበያ ዋጋ ንረት የታየበት እንደነበር ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ በአዲስ አበባ አራት ህዝባዊ ስብሰባዎችን አደረገ

“የኢህአዲግ ደጋፊዎች ሳይቀሩ “ብርቱካን ትፈታ” ብለው መጮህ አለባቸው” አቶ ስየ አብርሃ

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም. March 29, 2010)፦ መጋቢት 18 እና 19 ቀን በ4 የተለያዩ ሥፍራዎች የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጥምረት የሆነው መድረክ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂዷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...