”የአንድነትን ሕልውና የመታደግ ጥረታችንን ሕገወጥነት አይገታውም” እነፕ/ር መስፍን
እነኢ/ር ግዛቸው የፓርቲውን የምስክር ወረቀት፣ ጽ/ቤቱን፣ ማሕተሙን፣ ሰነዶችና ንብረቶች እንዲያስረክቡ ተጠየቁ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም. April 27, 2010)፦ እነፕ/ር መስፍን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን (አንድነትን) ሕጋዊነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ ጽሕፈት ቤቱን፣ ማሕተሙን፣ ሰነዶችና ንብረቶችን እንዲያስረክቧቸው፤ ማሕተሙን እንዳይጠቀሙና እንቅስቃሴአቸውን እንዲያቆሙ ትናንት ለኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው የፃፉላቸውን ደብዳቤ አልቀበልም ማለታቸውን አስመልክቶ፤ በዛሬው ዕለት ”የአንድነትን ሕልውና የመታደግ ጥረታችንን ሕገወጥነት አይገታውም” በሚል መግለጫ አወጡ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳና ሌሎችም ኢትዮጵያዊያን የኅሊና እስረኞች የከፈሉትና በመክፈል ላይ የሚገኙት መስዋዕትነት በገንዘብ ሊተመንና ከቶም ሊካካስ የማይችል መሆኑ ተገለጠ። ይህ የተገለጠው፣ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 6 ቀን 2010 በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት “ድጋፍና አክብሮት ለኅሊና እስረኞች” በሚል መርኅ በሂዩስተን ከተማ የተከናወነው በኢትዮጵያ የሚገኙ የኅሊና እስረኞች ማሰቢያና ድጋፍ ማሳያ ሥነሥርዓትን ያቀጋጀው ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ ላይ ነው።
ሙሉ ታሪኩን የያዘ መጽሐፍ ይመረቃል፣ በስሙ አደባባይ ይሰየማል 


