በቤንሻንጉል ጉሙዝ 12 ንጹኀን ተገደሉ

Demeke Mekonen

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነዋሪው ትጥቅ መታጠቅ አለበት አሉ

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪ ራሱን አደራጅቶ አስፈላጊውን ትጥቅ ታጥቆ የተጠናከረ መከላከል መገንባት አማራጭ የሌለው መኾኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። በዞኑ ትናንት ሌሊት 12 ንጹኀን ተገድለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ ዳውድ መግለጫ በጸጥታ ኃይሎች መቋረጡ ተነገረ

Dawud Ibas

በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የለም

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በቅርቡ በኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከኦነግ ሊቀመንበርነታቸው ተነስተዋል የተባሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በመኖሪያ ቤታቸው ሊሰጡ የነበረው መግለጫ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች መቋረጡ ተነገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘምዘም ባንክ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ ባንክ ኾነ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ (በግራ) ለዘምዘም ባንክ ሥራ መጀመር የሚችልበትን ፍቃድ በሰጡበት ወቅት

ብሔራዊ ባንክ ፍቃዱን አስረከበው
ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ የተፈረመ ካፒታል አሰባስቧል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ሲንቀሳቀስ የቆየው ዘምዘም ባንክ ሥራ ለማስጀመር የሚያስችለውን ፍቃድ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ከብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተረከበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳይያስ አፈወርቂ ጅማ ናቸው

Presidant Isaias Afwerki and PM Dr. Abiy Ahmed

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሏል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን፤ አቀባበል የተደረገላቸው በጅማ ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውዝግብ ውስጥ ባሉት የኦነግ አመራሮች ጉዳይ በምርጫ ቦርድ ተይዟል

ምርጫ ቦርድ፣ አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ እገዳውን ካሳለፉት አመራሮች ሦስቱ

ከኦነግ የተለያዩ አካላት በቀረበለት አቤቱታ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ እሰጣለሁ አለ

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 9, 2020)፦ በኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል በተፈጠሩ አለመግባባቶች ከተለያዩ የፓርቲው አካላት ሲደርሱት በነበሩት አቤቱታዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2013 ዓ.ም. 3ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 3rd, 2013 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሦስተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከመስከረም 18 - 24 ቀን 2013 ዓ.ም.) ያሳለፍነው ሳምንት የተለያዩ አገራዊና አነጋጋሪ የሚባሉ ክንውኖችን ያስተናገደ ነበር። ዐበይት እና ትኩረት ካገኙ ዜናዎች ውስጥ ሰኞ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የሚያካሔዱ መኾኑን ተከትሎ በተለይ ከትግራይ እየተሰማ ያለው ተቃውሞ ተጠቃሽ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአቶ ልደቱ ጉዳይ ፖሊስ የፍርድ ቤት ውሳኔ አለመፈጸሙ አነጋጋሪ ኾኗል

Lidetu Ayalew
  • ፖሊስ ከሕግ በላይ መኾኑን ያሳየበት ነው ተባለ

  • ጉዳዩ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሻ ስለመኾኑ ተመጠቆመ

ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 8, 2020)፦ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት አቶ ልደቱ አያሌው በመቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀው ጉዳያቸውን በውጭ ኾነው እንዲከታተሉ ያጸናው ውሳኔ እስካሁን አለመተግበሩ አነጋጋሪ ኾኗል። ፖሊስ ከሕግ በላይ መኾኑን ያሳየበት ነው ተብሎ እየተተቸ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመተከል ሽብር ሲፈጥሩ ነበሩ የተባሉ 14 ታጣቂዎች ተገደሉ

ጋሹ ዱጋዝ

ታጣቂዎች አንድ የውጭ ዜጋን ጨምሮ አሥራ አራት ንጹኀንን ገድለዋል

ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 8, 2020)፦ በተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ሲስተዋልበት በቆየው የመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ሽብር ሲፈጥሩ ነበሩ የተባሉ 14 ታጣቂዎችን መግደሉንና ሁለት መማረኩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ ቦርድ አባሉ የስንብት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

ምርጫ ቦርድ

የስንብቱን ደብዳቤ የጻፉት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ናቸው

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 7, 2020)፦ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባልነታቸው በፈቃዳቸው እንደሚለቁና ይህንንም ጥያቄያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ዶ/ር ጌታሁን ካሣ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ መሰናበታቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ክልል ምክር ቤት ላይ የተላለፈው ውሳኔ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጠበት

አደም ፋራህ
  • የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ አያደርግም

  • የፌዴራል ተቋማት ከክልሉ ተቋማት መረጃ መለዋወጥ አይችሉም

  • ከቀበሌ፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወሰናል

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 7, 2020)፦ የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ክልል ምክር ቤትና የክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካላት ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በኾነ ምርጫ የተቋቋሙ በመኾኑ፤ ለእነዚህ አካላት የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጐማ ማድረግ እንደማይችል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ