ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ ችሎት ሊሰየም ነው

ጉዳዩም የ”ጠንቋይ” ታምራት ነው

Ethiopia Zare (እሁድ መጋቢት 27 ቀን 2001 ዓ.ም. April 5, 2009)፦ ”በጥንቆላ መሥሪያ ቤቶቹ” ከሌሎች ስድስት ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን ”ባለአውሊያ” እና ”ባለከራማ” ነኝ በማለት የሰው ግድያ ወንጀልና ከባድ ማታለል ፈጽሟል በሚል በአቶ አቶ ታምራት ገለታ እና በተባሪዎቹ ላይ ክስ ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ ያሉን የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቤ ጨርሻለሁ የቀረኝ የቪዲዮ ማስረጃ ነው በማለቱ፤ በፍርድ ቤት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ ዕለት ተሰይሞ በዝግ ችሎት ቪዲዮ ካሴት ሊመለከት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ራሱን የገደለው ባለሀብት ንብረት በ58.5 ሚሊዮን ብር ዕዳ ሊሸጥ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. March 31, 2009)፦ ከወራት በፊት ራሳቸውን ከገደሉት ባለሀብቶች ውስጥ የ”ጌታነህ ትሬዲንግ” ባለቤት የነበሩትን የአቶ ዮሐንስ ጌታነህ ንብረት አቢሲኒያ ባንክ በ58 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ዕዳ የሐራጅ ሽያጭ አወጣበት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ባህላችን ለባርነት እንድንመቻች አድርጎናል” ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. March 30, 2009)፦ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በስዊድንና በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2001 ዓ.ም. በስቶክሆልም ከተማ በኢትዮጵያ ወቅታዊና ታሪካዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ የተለያዩ ሃሳቦች የተንሸራሸሩበት፣ ትምህርታዊ፣ አዝናኝና ታሪካዊ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አነጋጋሪው የጠንቋዩና የግብረአበሮቹ ክስ

ጠንቋዩና ስድስት ግብረአበሮቹ የተከሰሱት በ9 ሰዎች ሕይወት ማጥፋት፣ የሰው ገንዘብና ንብረት በማታለልና በማጭበርበር፣ ሴቶችን በመድፈር ነው

ከዕድሜ ልክ እስራት እስከ የሞት ቅጣት ሊቀጡ ይችላሉ

ጠንቋዩን ታዋቂ ግለሰቦችና ባለሥልጣኖች ያመልኩታል

ማንአልቦሽ ዲቦ፣ ብርቱካንና የሺመቤት ዱባለ፣ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ደንበኞቹ ነበሩ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ.ም. March 27, 2009)፦ ከአሥር ዓመታት በላይ ”ባለ አውሊያ” እና ”ባለ ከራማ” እንደሆነ በመግለጽ በርካታ ተከታዮችን አፍርቶ የነበረውና በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ያለው አቶ ታምራት ገለታ የተባለው ”ጠንቋይ” ጉዳይ በመዲናዋ አዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የሰሞኑ የመነጋገሪያ አጀንዳ (Hot issue) ሆኗል። መነጋሪያነቱ የጨመረው ታዋቂ አርቲስቶች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ አትሌቶች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ታዋቂ ባለሀብቶችና የኃይማኖት አባቶች በጥንቆላ ቤቶቹ ተጠቃሚ ነበሩ የሚሉ ምስክሮች ፍርድ ቤት በመቅረባቸው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መኢአድ መድረክን ለመቀላቀል ጥያቄ አቀረበ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ.ም. March 27, 2009)፦ በኢንጅነር ኃይሉ ሻውል የሚመራው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ (መድረክን) ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቡን የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ወቅታዊና መፃይ ጉዳዮች ላይ ሴሚናር ተካሄደ

Prof. Mesfin W.Mariam, 090326 Sweden (Photo S)ፕ/ር መስፍን በቀንዱና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ጽሑፍ አቀረቡ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2001 ዓ.ም. March 27, 2009)፦ በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ሀገሮች ላይ ባተኮረውና ኀሙስ መጋቢት 17 ቀን በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተደረገ የአንድ ሙሉ ቀን ሴሚናር ላይ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስኃቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ነበር። ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በሁለት ርዕሰ ጉዳዮ ጽሑፍ አቀረቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መስፍን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

Ethiopia Zare (ኀሙስ መጋቢት 17 ቀን 2001 ዓ.ም. March 26, 2009)፦ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባለሥልጣናት፣ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ከፓርላማ አባላት ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ተወያዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ፓርቲ ህዝባዊ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

በቅርቡም ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚጠራ ታወቀ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. March 25, 2009)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. ታላቅ የህዝብዊ ስብሰባ እንደሚጠራና ከህዝብ ጋር የሕግ የበላይነት መከበርን አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በኢምፔሪያል ሆቴል እንደሚያካሂድ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውይይት ለሰላምና ለጋራ አላማ በኢትዮጵያ

ታላቅ የስብሰባ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ

Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. March 25, 2009)፦ ባለፈው ዓመት መጨረሻ የተጀመረውና በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በየሶስት ወሩ የሚደረገው የውይይት መድረክ ቀጣይ የውይይት ርእሶችን በማዘጋጀት ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ተገለጸ። የመጀመሪያው ውይይት “ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የፕራዜዳንታዊ ውድድር ኢትዮጵያዊያን ምን ልንማር እንችላለን?” የሚል ነበረ ሲሆን በስብሰባው ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው እንደነበር አይዘነጋም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...