ለዓለም አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ቅድመ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ

በማትያስ ከተማ

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 4 ቀን 2001 ዓ.ም. January 12, 2009)፦ የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን፣ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን፣ የአቶ በቀለ ጅራታን እንዲሁም በፖለቲካ ምክንያት በእስር እየማቀቁ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈቱ የሚጠይቀውንና ረቡዕ ጥር 6 ቀን (January 14) ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሠልፍ በስዊድን ቅድመ ሁኔታው መጠናቀቁ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በወ/ት ብርቱካን እስር ዙሪያ የተጠናከረ ዘገባ

W/o Almaz G/Egziabeher“ሰው ገብቶ እንዲጠይቃት ይፈቀድልኝ” ወ/ሮ አልማዝ ገ/እግዚአብሔር የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እናት

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ወ/ት ብርቱካንን እንዳይጎበኝ ተከለከለ

ወ/ት ብርቱካን የታሰሩት የአንድነት ፓርቲን እንቅስቃሴ ለማዳከም ታስቦ ነው

የእንግሊዝ ኤምባሲ የወ/ት ብርቱካን እስር እንዳሳሰበው ገለፀ

“የሕገመንግሥቱ አንቀጽ 21 ሊከበርላቸው ይገባል” አቶ አበበ ወርቄ የኢሰመጉ ሊቀመንበር

መድረክ የወ/ት ብርቱካንን መታሰር አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ 

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 4 ቀን 2001 ዓ.ም. January 12, 2009)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ሊቀመንበር፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እናት የ72 ዓመቷ ወ/ሮ አልማዝ ገ/እግዚአብሔር፣ “በሕግ ስለተያዘው ጉዳይና ስለፖለቲካ የማውቀው ጉዳይ የለኝም፤ ግን ለሌላው እንደተፈቀደው ለልጄም ሰው ገብቶ እንዲጠይቃት ይፈቀድልኝ” ሲሉ መንግሥትን ተማፀኑ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ያሉ የግል ጋዜጦች በድምፅ አልባ መሣሪያ ተመቱ

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥር 1 ቀን 2001 ዓ.ም. January 09, 2009)፦ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጋዜጦች የሚታተሙበት ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት፣ ወደ 12 በመቶ የሚሆን የዋጋ ጭማሪ አደረገ። በርካታ አሣታሚዎች ጭማሪው ፕሬሶችን “ወደ ጉድጓድ የሚከት ነው፣ ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል” ብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እስረኞችን በሚመለከት ዓለም አቀፍ ሠላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና ቴዲ አፍሮ በጉልህ ይጠቀሳሉ

በሲያትል ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. January 06, 2009)፦ ያለአግብብ የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ታላቅ ዓለማቀፍ ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና በተለይ እውቁን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮንና የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ድርጅት መሪ የሆነችውን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሁኔታ በጉልህ የሚያሳይ ዓለማቀፍ የአዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቋመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በወ/ት ብርቱካን እና በቴዲ አፍሮ እስራት ቁጣቸውን ገለጹ

Protest @ Ethiopian Embassy in Sweden, Stockholm,20090105Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. January 05, 2009)፦ ሰኞ ዕለት በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳንና የቴዎድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮ) አለአግባብ መታሰር፤ እየተፈጸመ ያለውንም ግፍና በደል፤ እንዲሁም የዲሞክራሲ መታፈንን፤ በመቃወም በስቶክሆልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት በራፍ ተገኝተው ቁጣቸውን ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነፃው ፕሬስ ማክተሚያ ተቃረበ

የሕትመት ዋጋን በመጨመር ነፃው ፕሬስ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ነው

Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. January 05, 2009)፦ በመንግሥት የሚተዳደረው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ከጥር አንድ ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ በጋዜጦች ላይ የሕትመት ዋጋ የሚጨምር ሲሆን፣ ከምርጫ 97 በኋላ የተቋቋሙት ጥቂት የፕሬስ ውጤቶች ከገበያ እንዲወጡ የሚያደርጋቸው መሆኑ ታወቀ። “ፕሬሱን ለማዳፈን የታለመ ነው” ተብሎ ተተችቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወ/ት ብርቱካን የአራት ዓመት ልጅ በቃሊቲ እስር ቤት ተንሰቅስቃ አለቀሰች

ወ/ት ብርቱካንን መጠየቅ አይቻልም፤ እናትና ልጃቸው ብቻ ተፈቀደላቸው

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. January 03, 2009)፦ ቅዳሜ ዕለት ወ/ት ብርቱካንን ቃሊቲ ወሕኒ ቤት ለመጠየቅ የሄዱ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ለረዥም ሰዓታት እንዲጠብቁ ከተደረገ በኋላ ገብተው እንዳይጠይቋቸው ተከለከሉ። የወ/ት ብርቱካን ወላጅ እናትና የአራት ዓመት ሕፃን ልጃቸው ብቻ ለ40 ደቂቃ አገኟቸው። ሕፃንዋ ልጃቸው ከቃሊቲ እስር ቤት ስትወጣ ተንሰቅስቃ አለቀሰች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ጠባብ ክፍል ውስጥ ታስረው የረሃብ አድማ ላይ ናቸው

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. January 02, 2009)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የፖለቲካ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትና የ34 ዓመቷ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከታሰሩበት ያለፈው ሰኞ ታህሳስ 20 ጀምሮ ሁለት በሁለት በሆነ ክፍል ውስጥ ለብቻቸው የታሰሩ ሲሆን፣ ላለፉት አምስት ቀናት በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...