በወ/ት ብርቱካን የሚመራው ላዕላይ ም/ቤት ስበሰባውን ለቅዳሜ አዛወረው

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 28,2008) በተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ሊያደርገው የነበረውን የላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባ ለነገ ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ማዛወሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባ ራጉዔል ቤ/ክ አካባቢ ቦንብ ፈነዳ

በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. / February 29,2008) ዛሬ ረፋዱ ላይ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ መርካቶ በሚገኘው ራጉዔል ቤተክርስቲያን አካባቢ "ቁጭራ" በሚባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አጠገብ ቦንብ ፈንድቶ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ይህንን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰዓት ድረስ በሰው ሕይወት ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለማወቅ አልቻልንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእነአቶ ተመስገን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ተጠየቀ

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29,2008)ማህተምና የጽህፈት ቤት መሳሪያዎች አላስረክብም ብለዋልና የነአቶ ተመስገን ዘውዴ ያለመከሰስ የፓርላማ መብት ይነሳልኝና ልክሰሳቸው በማለት አቶ አየለ ጫሚሶ ለፓርላማ ክስ አቀረቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቂም በቀል ተነሳሰቶ ጎረቤቱን የገደለው ግለሰብ እስካሁን አልተያዘም

• የሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል

• አንድ የክልል ባለሥልጣን ለገዳዩ ከለላ ሰጥቶታል ተብሏል

በሸዋዬ ካሳሁን

Ethiopia Zare (አርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008) ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ራያ ቆቦ በተባለው ከተማ በቂም በቀል በመነሳሳት የሰው ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ሊውል ባለመቻሉ በየሟች ቤተሰቦች ስጋት ላይ ወድቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድ ተማሪ ሞት ዲላ ዩኒቨርስቲ ተረበሸ

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. February 29, 2008)፦ ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ በምትገኘው ዲላ ከተማ ባለው «ዲላ ዩኒቨርስቲ» በተገደለ አንድ ተማሪ ምክንያት ዩኒቨርስቲው ተረበሸ። ተማሪውን ገድሎታል በሚል የተጠረጠረው ተማሪም በቁጥጥር ስር ውሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በዶ/ር ታዬ ይመራ የነበረው ኢመማ ለተለጣፊው ተሰጠ

ፍርዱ አግባብ አይደለም ያሉ መምህራን ታፈሱ

‘ውሳኔው ኢ-ፍትሀዊ ነው’ አቶ ገሞራው ካሣ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. February 27,2008)፦ በ1941 ዓ.ም. የተቋቋመውና ቀደም ሲል በዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት ይመራ የነበረው አንጋፋው የመምህራን ማህበር ከ15 ዓመታት የፍርድ ሙግት በኋላ በ1985 ዓ.ም. ለተመሰረተውና በኢህአዴግ ተቀጥላ ለሆነው ቡድን የተወሰነ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለካንሰር ሆስፒታል ግንባታ ኮንሰርት ይዘጋጃል

(ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2000 ዓ.ም. February 25,2008)፦ በኢትዮጵያ ትልቁንና የመጀመሪያውን የካንሰር ሆስፒታል ለመገንባት የገቢ ማሰባሰቢያ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ኮንሰርት በሚሌኒየም አዳራሽ ይዘጋጃል፡፡

ላይፍ ሰከንድ ቻንስ ፋውንዴሽን ከሠራዊት መልቲ ሚዲያ ጋር በመተባበር በየካቲት 22 ቀን 2000 .ም. በሚሌኒየም አዳራሽ የሚደረገው ኮንሰርት ዓላማ፤ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሸኖ ከተማ ላይ ለሚገነባው የካንሰር ሆስፒታል የመጀመሪያውን የገቢ ማሰባሰቢያ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ይዘጋጃል፡፡ 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አፋኝ የሲቪል ማኅበረሰብ ረቂቅ አዋጅ ወጣ

የሕግ ባለሙያዎች እያወገዙት ነው

Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 16 ቀን 2000 ዓ.ም. February 24,2008) በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ ሰሞኑን የተለቀቀው የሲቪል ማኅበረሰብ ረቂቅ አዋጅ አፋኝ ይዘት ያለው ነው ሲሉ አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት ሰጡ።

የሕግ  ባለሞያና የሲቪል ማኅበረሰብ አባል እንደገለጹት፤ በሕግ ማርቀቅ ሂደት የሲቪል ማኅበረሰቡና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እንዲሳተፉ በመንግሥት በኩል ፈቃደኝነት እንዳልነበረ ገልጸው፤ አሁንም ቢሆን ወጣ የተባለውን ረቂቅ አዋጅ ከድረ-ገጽ ላይ ወስዶ ከማየት ውጭ በመንግስት በኩል የተገለጸ ምንም ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰለፊያና የአልቁዱስ ጋዜጣ አዘጋጆች ታሰሩ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2000 ዓ.ም. February 23,2008) የ"ሰለፊያ" ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ኢብራሂም መሐመድ እና የ"አልቁዱስ" ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ኢዘዲን መሐመድ የካቲት 8 ቀን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አንድ ዘገባ ጠቆመ።

የአልቁዱስ አሣታሚና የአቶ ኢዘዲን መሐመድ ባለቤት ወ/ሮ ማሪያ ቃዲም ከባለቤታቸው ጋር ታስረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...