የኢሕአዴግ መንግስት ለአምባሳደሩ መታሰር በቂ መልስ አላቀረበም

“የዓለም አቀፍ ህግጋትን ጥሰዋልየስሎቫክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር

Ethiopia Zare ( ቅዳሜ ኅዳር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. November 19, 2011)፦ አጠያቂ በሆነ መልኩ በኢህአዴግ ታጣቂ የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ለ3 ቀናት በእስር የቆዩትን አምባሳደር በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት እጅግ ዘግይቶ የሰጠው ምላሽ አጥጋቢ አይደለም ሲሉ የስሎቫክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አወገዙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አድባር በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የተሳካ ውይይት አደረገ፡

የመምህር የኔሰው መስዋእትነት ተዘከረ፡ ሁለት ወጣት ምሁራን የጥናት ስራዎች አቀረቡ

Ethiopia Zare (አርብ ኅዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. November 18, 2011)፦ አድባር በመባል የሚታወቀው የውይይትና ክርክር ክበብ በቶሮንቶ የተሳካ ውይይት ከማድረጋቸውም በላይ ‘ፍትህና ነጻት በሌለበት ሀገር መኖር ሰለቸኝ” በማለት ራሱን በእሳት ያቃጠለው መምህር የኔሰው ገብሬ መስዋእትነት በታላቅ ሁኔታ ተዘከረ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) ወደ ኬንያ ተሰደደ

Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2004 ዓ.ም. November 14, 2011)፦ በአውራምባ ታይም፣ በተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ላይ ወጋወጎችን በመጻፍ የሚታወቀው ጋዜጠኛ አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) በደህንነት ሰዎች በደረሰበት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና ክትትል ከሀገሩ ተሰዶ በጎረቤት ሀገር ኬንያ እንደሚገኝ ምንጮች ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌ አንድ ላይ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

ናትናኤል መኮንን ክፉኛ መደብደቡን ለፍርድ ቤት ገለጸ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. November 10, 2011)፦ ልደታ በሚገኘው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ የቀረቡት ስምንት ተከሳሾች መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጎ አንድ ላይ በካቴና ተጠፍረው መቅረባቸውና የአንድት ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆነው ናትናኤል መኮንን በፖሊሶች ክፉኛ መደብደቡን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወደ እስራኤል የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን በሲና በረሃ ቀልጠው እየቀሩ ነው

የሰወነት አካላቸው በጥቁር ገበያ ይቸበቸባል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 25 ቀን 2004 ዓ.ም. November 5, 2011)፦ በግብጽ በኩል አቋርጠው ወደ እስራኤል ሀገር ለመሻገር የሚሞክሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ሱዳናዊያን ስደተኞች የሰውነት አካላቸው እየተሰረቀ እሬሳቸው በበረሃ ውስጥ እንደሚጣል ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በመረጃ አረጋገጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ በፑንትላንድ የሞት ቅጣት ለተወሰነበት ኢትዮጵያዊ 700ሺህ ብር ከፈለ!

Ethiopia Zare ( ቅዳሜ ጥቅምት 18 ቀን 2004 ዓ.ም. October 29፣ 2011)፦ በሶማሊያዋ ፑንትላንድ በጎሳ መሪዎች የሞት ወይንም የ700 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ለተወሰነበት አስመሮም ኃይለስላሴ እውቁ የሙዚቃ ሰው ቴዎድሮስ ካሳሁን የገንዘብ ቅጣቱን እንደከፈለለት ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮሎኔል መንግስቱ ደህንነት አጠያያቂ ሆኗል

ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በዚምባብዌ እስር ቤቶች ይደበደባሉ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. October 27, 2011)፦ የኮ/ል ጋዳፊን ሞት ተከትሎ በዚምባብዌም የቀድሞው መሪ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም የደህንነነት ጥበቃ ጉዳይ ህዝቡን እንደ አዲስ ማነጋገር ጀምሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዳፊ በምስጢር በተያዘ ቦታ ሊቢያ ውስጥ ተቀበሩ

የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ Muammar Gaddafiየሙአመር ኧል ጋዳፊ ቀብር እና የደጋፊዎቻቸው አስተያየት

የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ በሊቢያ በአንድ በምሥጢር በተያዘ ቦታ መቀበራቸው ተገለጸ። ጋዳፊ፣ ልጃቸው ሙዋታሲም እና የመከላከያ ሚንስትራቸው አቡ በከር ዩኒስ ጃበር ጥቂት ቤተዘመድ እና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ንጋት ላይ በእሥላማዊው ኃይማኖት ደንብ መሠረት ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን የሽግግሩ ብሔራዊ ምክር ቤት አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ