አቶ በረከት ስምዖን በአል ጀዚራ ተፋጠጡ

  • ”እንዲህ ያለ የምርጫ ውጤት በአምባገነኖች ብቻ የሚካሄድ ነው፤ ውጤቱ በሠላማዊ ትግል የሚያምኑትን ሲያኮማሽሽ፣ በትጥቅ ትግል የሚያምኑትን ያበረታታል፤ በዚህም ምክንያት ጦርነት በአካባቢው ቢጀመር ለዓለምም ሆነ ለአካባቢው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ሊያስከትል ይችላል” አቶ ጀዋር መሐመድ (ተመራማሪ)
  • ”ህዝቡ መርጦናል” አቶ በረከት ስምዖን
  • ”መራጮች ወደ ምርጫ ሲሄዱ ከፍተኛ ጥልቀት ባለው ፍርሃት ተሸብበው እንደነበር ለመገመት አያስቸግርም” ሌስሊ ሌፍኮ (ኒዩማን ራይትስ ዎች)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም. May 27, 2010)፦ ዛሬ የአል ጀዚራ እንግሊዝኛ ቴሌቭዥን ጣቢያ የአቶ መለስ ዜናዊን ቀኝ እጅና የመንግሥት የኮምዩኒኬሽን ሚኒስትር የሆኑትን አቶ በረከትን፣ በግል ተመራማሪና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለአል ጀዚራ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት አቶ ጀዋር መሐመድን ከዋሽንግተን፣ እንዲሁም ከሂዩማን ራይትስ ዎች ሌስሊ ሌፍኮን ከዋሽንግተን በ”ኢንሳይድ ስቶሪ” ፕሮግራሙ ባለፈው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. የተካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ አነጋግሯቸዋል። (ሙሉውን ውይይት ለማየትና ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

የአማርኛ እና የኢትዮጵያ ዕሴቶች ማስተማሪያ ዲቪዲ በለንደን ተመረቀ

በ3 ቋንቋዎች የተዘጋጁት ዲቪዲዎችግንቦት 7 2002 ዓ.ም. በለንደን ከተማ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሴንተር ሦስት የአማርኛ እና የኢትዮጵያ ዕሴቶች ማስተማሪያ ዲቪዲ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵውያን እና አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን በተገኙብት በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ‘ምርጫ’ እያወዛገበ ነው

“ምርጫው ይደገም” ተቃዋሚዎች

“የምርጫ ሥርዓትን የተከተለ አይደለም” ስቴት ዲፓርትመንት

በግል በብቸኝነት ለፓርላማ ያለፉት ከእግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ኢህአዲግ በጉልበት ያነሳቸው ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ናቸው

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 18 ቀን 2002 ዓ.ም. May 26, 2010)፦ በኢትዮጵያ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. በተካሄደው ‘ምርጫ’ ገዥው ፓርቲ በቅድመ ምርጫ ቆጠራ ማሸነፉን ካወጀ ወዲህ በተቃዋሚዎች፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና በአውሮፓ ታዛቢዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ተነገረ። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት መግለጫ አውጥቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳት “እሳት” ተባለ፤ የተመልካቾቹ ቁጥር እያሻቀበ ነው

“ኢሳት ሁለት ወር ቀደም ቢል ኖሮ ምርጫው የኛ ይሆን ነበር” አስተያየት ሰጪዎች

በተክለሚካኤል አበበ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የተከታታዮቹ ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ከምርጫው በፊት ቢጀመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርግ እንደነበር ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአባ ጳውሎስ ወኪል አባ ማትያስ ንጉሴ ወደ ቫንኩቨር ሊያቀኑ ነው

Aba Matiasበቫንኩቨር ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. May 20, 2010)፦ በቶሮንቶ ካናዳ የአባ ጳውሎስ ቀኝ እጅ የሆኑት አባ ማትያስ ንጉሴ ደስታ በዚህ በያዝነው ሣምንት (ሜይ 23-24) በህሆተ ሰማይ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ጋባዥነት ወደ ቫንኩቨር እንደሚመጡና ቤተክርስቲያኗ ወደ አባ ጳውሎስ ስር እንድትገባ ተግተው ሲሰሩ የነበሩት ሰዎችም አባ ማትያስን ለመቀበል ሽር ጉድ እያሉ እንደሆነ ምንጮች ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በተንቤን የአቶ ስየ ቅስቀሳ ችግር ገጥሞታል

Ato Seye AbrhaW/o Aregash Adaneወ/ሮ አረጋሽ በአድዋ የጠሩት ስብሰባ ብጥብጥ አስነሳ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 12 ቀን 2002 ዓ.ም. May 20, 2010)፦ ከሦስት ቀናት በኋላ ከፍተኛ የ‘ምርጫ’ ፉክክር ይካሄድበታል ተብሎ በሚጠበቀው በትግራይ ክልል በተምቤን እና አድዋ ወረዳዎች አቶ ስየ አብርሃ እና ወ/ሮ አረጋሽ በሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ከፍተኛ ወከባ እየገጠማቸው መሆኑን ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ በመስቀል አደባባይ የጠራው ስብሰባ ተከለከለ

በደብረዘይትና በአዲስ አበባ የመጨረሻ ቅስቀሳውን ያካሂዳል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 7 ቀን 2002 ዓ.ም. May 15, 2010)፦ መድረክ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 7 ቀን 2002 ዓ.ም. (ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም.ትን በማሰብ) በመስቀል አደባባይ ሊጠራው ያሰበው ህዝባዊ ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የመድረክ አባላት አንድ ፖሊስ ገደሉብኝ” የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. May 9, 2010)፦ በዛሬው ዕለት የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን በመጥቀስ፤ ”በመድረክ ፓርቲ የተደራጁ ሦስት ግለሰቦች አንድ ፖሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ወግተው ገደሉ” በማለት መዘገባቸው ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አስረዳ። ሙሉውን አስነብበኝ ...