የኮሎኔል መንግስቱ ደህንነት አጠያያቂ ሆኗል

ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በዚምባብዌ እስር ቤቶች ይደበደባሉ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. October 27, 2011)፦ የኮ/ል ጋዳፊን ሞት ተከትሎ በዚምባብዌም የቀድሞው መሪ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም የደህንነነት ጥበቃ ጉዳይ ህዝቡን እንደ አዲስ ማነጋገር ጀምሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዳፊ በምስጢር በተያዘ ቦታ ሊቢያ ውስጥ ተቀበሩ

የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ Muammar Gaddafiየሙአመር ኧል ጋዳፊ ቀብር እና የደጋፊዎቻቸው አስተያየት

የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ በሊቢያ በአንድ በምሥጢር በተያዘ ቦታ መቀበራቸው ተገለጸ። ጋዳፊ፣ ልጃቸው ሙዋታሲም እና የመከላከያ ሚንስትራቸው አቡ በከር ዩኒስ ጃበር ጥቂት ቤተዘመድ እና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ንጋት ላይ በእሥላማዊው ኃይማኖት ደንብ መሠረት ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን የሽግግሩ ብሔራዊ ምክር ቤት አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዲያስፖራ ኢትዮጵያ ሰላዮችን እናጋልጥ!

EMF -- የኢትዮሜዲያ ድረ-ገጽ "Bad news for Meles Zenawi spies in the U.S." ብሎ ባሰፈረው ዜና የቨርጂኒያው መሃመድ አናስ ሱኢድ ለሶሪያ አንባገነን መንግሥት ሲሰልል ተይዞ መታሰሩን ገልጾ፤ ይህም በዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ካገኙ በኋላ ለአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ለሚሰልሉ የገዢው ፓርቲ አገልጋዮች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አስፍሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

እስረኞቹ ከአንድ ወር በኋላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አይተዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም. October 13, 2011)፦ በማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተወሰደባቸውና በሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ሌሎች እስረኞች በድጋሚ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ተመልሰዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ በሶማሌ ላንድ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ስደተኞች እንዲታፈሱለት ጠየቀ

300 የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስደተኞች በሀርጌሳ ታስረዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. October 8, 2011)፦ የኢህአዴግ መንግስት በሱማሌ ላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች ታፍነው እንዲመለሱለት ትእዛዝ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት እስካሁን 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሰሳ ተይዘው በሀርጌሳ እስር ቤቶች ውስጥ የታጎሩ ሲሆን በቅርቡም ወደ አዲስ አበባ ይላካሉ ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአምባሣደር ዘውዴ ኃይለማርያም ሥርዓተ ቀብር በስቶክሆልም ተፈጸመ

Ambassador Zewde HaileMariamEthiopia Zare (ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2004 ዓ.ም. September 26, 2011)፦ አምባሣደር ዘውዴ ኃይለማርያም በደረሰባቸው ሕመም ስቶክሆልም በሚገኘው ካሮሊንስካ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ነኀሴ ፴ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. በ፹ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሥርዓተ ቀብራቸውም ረቡዕ መስከረም ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ሶልና በሚገኘው በኖራ ግራቭኒንግስ ፕላትስ ተፈጽሟል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች መግለጫ አወጡ

እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬና ርዕዮት ዓለሙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም 15 ቀን 2004 ዓ.ም. September 26, 2011)፦ በነፃ ፕሬስ ላይ በሚደረገው ጫና፣ እስርና እንግልት ምክንያት በስደት ላይ የሚገኙ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች በ’ሽብርተኝነት’ ስም በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙ ላይ የተፈጸመውን እስር አወገዙ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

”በሽብርተኝነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!” መድረክ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 13 ቀን 2004 ዓ.ም. September 24, 2011)፦ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ፣ የኦፌዴን ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የኦህኮ የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳ፣ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ናትናኤል መኮንንና አቶ አሳምነው ብርሀኑ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፣ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ፣ ጋዜጠኛ ስለሽ ሐጎስ እንዲሁም አርቲስት ደበበ እሸቱ የአንባገነናዊው ሥርዓት ጅምላ እስራት ሰለባ ከሆኑት ጥቂቶቹ መሆናቸውን መድረክ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው መግለጫ ገለፀ። ሙሉውን አስነብበኝ ...