ቴዲ አፍሮ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተለቀቀ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. August 13, 2009)፦ ላለፉት 484 ቀናት በእስር የቆየው ወጣቱ እውቅ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30 አካባቢ ከእስር መለቀቁን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. August 13, 2009)፦ ላለፉት 484 ቀናት በእስር የቆየው ወጣቱ እውቅ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30 አካባቢ ከእስር መለቀቁን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
መጻሕቶቹን ለላይብረሪ፣ ልብሶቹን ለእስረኞች አከፋፈለ
Ethiopia Zare (ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. August 13, 2009)፦ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. ጠዋት ከእስር እንደሚለቀቅ በስፋት ተወርቶ የነበረ ቢሆንም፤ አድናቂዎቹና ቤተሰቦቹ ቃሊቲ እስር ቤት ሄደው ለረዥም ሰዓታት ሲጠባበቁ ከቆዩ በኋላ ባዷቸውን ተመልሰዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ዓቃቤ ሕግ በሞት ይቀጣልኝ ሲል ጠየቀ
Ethiopia Zare (ረቡዕ ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. August 12, 2009)፦”ባለአውሊያ” እና ”ባለከራማ” ነኝ በማለት ከአሥር ዓመት በላይ በጥንቆላ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው አቶ ታምራት ገለታን ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. የዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ”ጥፋተኛ” ያለው ሲሆን፣ ንብረቶቹም ተወርሰው ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ ወሰነ። ዓቃቤ ሕግ በሞት ይቀጣልኝ አለ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፍርዱ ከአሜሪካን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ ለማድረግ እንደሆነ ተጠቁሟል
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 30 ቀን 2001 ዓ.ም. August 6, 2009)፦ ለሕክምና በአሜሪካ ሀገር በሚገኙት ታዋቂው ጠበቃ አበበ ወርቄ ላይ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ከኤቢሲ ብሮድካስቲን ጋር በተያያዘ የአንድ ዓመት እስራትና የገንዘብ ቅጣት ወሰነባቸው። ቅጣቱ አቶ አበበን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ ለማድረግ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለፁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ከ46ቱ ተከሳሶች በእስር የሚገኙት 32ቱም ይከላከሉ ተባሉ፣
በሌሉበት ከተከሰሱት 13ቱ ጥፋተኛ ተባሉ
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 30 ቀን 2001 ዓ.ም. August 6, 2009)፦ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 30 የዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት፤ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ውስጥ የግንቦት 7 መሥራቾችና መሪዎች በሆኑት በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና በአቶ አንደርጋቸው ጽጌ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ። በእስር ላይ ከሚገኙት 32 ተከሳሾች ውስጥ 29ኙን በቀረቡባቸው 5ቱም ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. August 5, 2009)፦ ፕ/ር መስፍንን ጨምሮ 21ዱ የታገዱት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት “የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሥልጣን መባለግ” በሚል በተከታታይ ሲያወጡት የነበረውን መግለጫ ክፍል ሦስት አወጡ። ይኸው መግለጫ “በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ደንባዊና ተቋማዊ አሠራር ሲፈተሽ” የሚል ንዑስ ርዕስ ሰጥተውታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. August 3, 2009)፦ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነውና የካናዳ ዜግነት ያለው አቶ በሽር ሙኽታል በኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነትና በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ ክስ ተመስርቶበት ሲከራከር ከቆየ በኋላ፤ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. የዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንደፈረደበት የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ዘገበ።
Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. July 31, 2009)፦ የጤና ጥበቃ መ/ቤት፤ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፣ መንግሥትና ህዝብ ከእነሱ የሚጠብቀውን ተግባር አልፈጸሙም በማለት በርካታ የጤና ባለሙያዎች ሕግ ፊት ለማቅረብ እንደሚፈልጋቸው አስታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአባ ጳውሎስ ልዩ የጥበቃ ሹም ቃላቸውን ሰጡ
Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. July 31, 2009)፦ ለጥቅምት ወር 2002 ዓ.ም. ቀጠሮ የተያዘለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ውዝግብ በአሁኑ ወቅትም መልክና ቅርፁን ለውጦ በመንቀሳቀስ ላይ ነው። በዚሁ ውዝግብ ከአቶ አባይ ፀሐዬ ቀጥሎ አቶ በረከት ስምኦንም እጃቸውን ማስገባታቸው ታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ሐሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. July 30, 2009)፦ በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ከተማ የዝርፊያ፣ የቅሚያና የሥርቆት ወንጀል ተግባሮች በአስከፊ መልኩ የጨመረ ሲሆን መሠል ወንጀሎች አስቀድሞ በብዛት ይታዩባቸው ከነበሩት ሥፍራዎች ባልተናነሰ ሁኔታ በሌሎችም የከተማይቱ ክፍሎች በሰፊው እየተሰተዋሉ ናቸው፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...