ምሥራቅ ኢትዮጵያ ለድርቅ አደጋ ተጋልጧል

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. July 24, 2009)፦ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ድርቅ ተባብሶ ቀጥሏል። ከመስከረም ወር 2001 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ድረስ ከአስቦት እስከ ካራሚሌ ባለው 130 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የዝናብ ዘር አለመታየቱን የሜኤሶ የበሮዳ እና የአጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ሊቋረጥ ነው

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. July 24, 2009)፦ ”ድሃን ማቆር” እየተባለ የሚነገርለት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በመጪው ዓመት ሊቋረጥ መሆኑ ታውቀ። የባንክ ምንጮች እንደገለጹት መንግሥት በአጋጠመው የገንዘብ ቀውስ ምክንያት ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉት የክልል ከተሞች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ይቋረጣል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲኖዶሱ ወሳኙን አጀንዳ ለጥቅምት ቀጠረ

አንድ ጳጳስ በለሊት ደህንነት ቢሮ ተወሰዱ

የጳጳሳት መኖሪያ ቤት በምሽት ተደብድቧል

ፓትርያርኩ ሕገ ቤተክርስቲያን አላውቅም አሉ

(ልዩ ሪፖርታዥ)

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. July 18, 2009)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርኩ በሥራ አስፈጻሚው ላይ የጣሉትን እግድ እንዲያነሱ ውሳኔ አሳለፈ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ፓርቲ 21ዱን አመራር አባላት አላገድኩም አለ

የተሰራጩት መግለጫዎችና ዘገባዎች የፓርቲውን ደጋፊዎች አምታትተዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. July 17, 2009)፦ በተለየም በዚህ በያዝነው ሣምንት ”አንድነት ለዲሞክረሲና ለፍትህ” የተሰኘውን ፓርቲ አስመልክቶ በተለያዩ የኢትዮጵያውያን መገናኛ ብዙኀን የመሰነጣጠቅ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑን ተዘግቧል። በሣምንቱ ማብቂያ ላይ የድርጅቱን አለመሰንጠቅና ታግደዋል የሚባሉትን 21 የፓርቲውን አመራሮች አለመታገድ በሚመለከት መግለጫ ወጥቷል። ዘገባዎቹና መግለጫዎቹ የፓርቲውን ደጋፊዎች አመታትዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ማንም ከፓርቲው ህልውና በላይ ሊሆን አይችልም" ዶ/ር ኃይሉ አርአያ (ሪፖርተር ጋዜጣ)

"ከዚህ በኋላ ዝም አንልም" እነፕሮፌሠር መስፍን

በአሰግድ ተፈራና ኃይሌ ሙሉ

(ሪፖርተር ጋዜጣረቡዕ ሐምሌ 7 ቀን 2001 ዓ.ም.)፦ አንድነት ፓርቲ "ሥርዓት ጥሰዋል" ባላቸው የአመራር አባላቱ ላይ እርምጃ መውሰዱንና ይህም እርምጃ ወደ ፊት እንደሚቀጥል፣ ማንም ከፓርቲው ህልውና በላይ ሊሆን እንደማይችል የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለሪፖርተር ገለፁ። እነፕሮፌሠር መስፍን "የአንድነት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሥልጣን መባለግ" በሚል ርዕስ ባወጡት ጽሑፍ የሥራ አስፈፃሚውን የአሰራር ብልሹነት "ከዚህ በኋላ ዝም አንልም" ብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀነኒሳ በቀለ አራተኛውን የጎልደን ሊግ አሸነፈ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ Kenenisa Bekeleቀሪዎቹን ሁለቱን ካሸነፈ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩ ተቋዳሽ ይሆናል

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. July 17, 2009)፦ እ.ኤ.አ. የ2009ኙ ጎልደን ሊግ አራተኛ ውድድር በፓሪስ ፈረንሣይ እየተካሄደ ሲሆን፣ ይህ ዜና ከመጠናከሩ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ3000 ሜትሩን ውድድር በ7 ደቂቃ ከ28፡64 ሰከንድ በመጨረስ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቋል። ከዚህ በኋላ የሚደረጉትን ሁለት ውድድሮች በአሸናፊነት ካጠናቀቀ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩ ጃክ ፖት ተቋዳሽ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቪኦኤው ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሃ ነፃ ተሰናበተ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. July 15, 2009)፦ ያለቀረጥ የገቡ የህትመት መሣሪያዎችን አላግባብ መጠቀምና ለመሸጥ መሞከር በሚል ክስ የቀረበባቸው የአዲስ ብሮድካስቲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤቶችና ዕቃውን ለማሻሻጥ ሞክረዋል የተባሉ ደላሎች ክሳቸው ሲታይ ውሎ የቪኦኤው ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሃ በነፃ የተሰናበተ ሲሆን፣ ሌሎቹ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ ዛሬ የዋለው ችሎት ብይን ሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የባሥልጣናት የሹም-ሽር በመስከረም ማግስት ይካሄዳል ተባለ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. July 15, 2009)፦ በአዋሳ ከተማ ከ10 ወር በፊት በተካሄደው የኢህአዲግ ጠቅላላ ስብሰባ ድርጅቱን በወጣት አመራር እገነባለሁ ያለው ገዥው ፓርቲ በመጪው መስከረም የህወሓት ኢህአዲግ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ ጡረታ የሚወጡ የድርጅቱ አንኳር ሰዎች መኖራቸው ተጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ተቀምጧል

የመንግሥት ባለሥልጣኖች በታዛቢነት ታድመዋል

Ethiopia Zare (አርብ ሐምሌ 3 ቀን 2001 ዓ.ም. July 10, 2009)፦ እየተካረረ የመጣውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ውዝግብ ለመፍታት በማሰብ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ፤ ዛሬ አርብ ሐምሌ 3 ቀን 2001 ዓ.ም. የመንግሥት ሁለት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በተገኙበት ማለዳ ላይ በቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...