የኢትዮጵያ ሚዲያ መድረክ ጊዜያዊ እክል ገጠመው

Kinfu Assefa, EMF webmaster & editor (Photo: Nazret.com)Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. April 25, 2009)፦ በውጭ ሀገር ከሚገኙት የኢትዮጵያውያን ድረ ገጾች ውስጥ በርካታ አንባቢዎች ያሉት የኢትዮጵያ ሚዲያ መድረክ (EMF) የተሰኘው ድረ ገጽ በዛሬው ዕለት ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት መታገዱን የድረ ገጹ አዘጋጅ አቶ ክንፉ አሰፋ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ። ለአንባቢዎቻቸውም የተከሰተውን ጊዜያዊ ችግር እስከሚስተካክሉ በትዕግስት እንዲጠባበቁ በአክብሮት ጠይቀዋል።  (ድረ ገጹ ይህ ዘገባ ከተነበበ ከግማሽ ሰዓት በኋላ መሥራት ጀምሯል)

የግንቦት ሰባት አባላት ናቸው የተባሉ 35 ሰዎች ታሰሩ

የግንቦት ሰባት አመራሮች (አቶ ቸኮል ጌታሁን እና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ)በጉዳዩ ላይ ግንቦት ሰባት መግለጫ ሰጥቷል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. April 25, 2009)፦ የግንቦት ሰባት አባላት ናቸው የተባሉ 35 ሰዎች በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። ይህን መግለጫ በማስመልከት ግንቦት ሰባትም መግለጫ ሰጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙዚቃ ንጉሡ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ አስከሬኑን ተሰናበተ

በኢትዮጵያ የቀብር ታሪክ ከፍተኛው ህዝብ የተገኘበት ነበር

የክቡር ዶ//ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ሥርዓተ ቀብር፣ ሚያዝያ 15 ቀን 2001 ዓ.ም.

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 15 ቀን 2001 ዓ.ም. April 23, 2009)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተለምዶ ፒኮክ በሚባለው ቦታ በሚገኘው የዝነኛው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ መኖሪያ ቤት ገና ከጠዋቱ በሰው ተጨናንቋል። “ቤተል” የተባለው የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት የቀብር ሥነሥርዓቱ ያማረ እንዲሆን ሽርጉድ ይዘዋል። ከቀኑ አምስት ሰዓት ተኩል ሲሆን አስክሬኑን ከቤቱ አጅቦ ለማውጣት በተፈጠረው የሰው ብዛት ምክንያት እጅግ አስቸጋሪ ነበር። (ከላይ ያለው ፎቶግራፍ ላይ በግራ በኩል ተደግፈውና አጎንብሰው የሚያለቅሱት የክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የቀድሞ ባለቤቱና የሁለት ልጆቹ እናት ወ/ሮ ማርታ ናቸው)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮና የዓቃቤ ሕግ የሰበር አቤቱታ ለችሎት መቅረብ አለመቅረቡን ለመወሰን ለግንቦት 14 ተቀጠረ

ቴዲ አፍሮ Teddy Afro ዓቃቤ ሕግ የስድስት ዓመቱ ቅጣት እንዲፀናበት ጠይቋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. April 22, 2009)፦ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መግቢያ በር ላይ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እናት ወ/ሮ ጥላዩ አራጌ (ራዬ)ን ጨምሮ በርካቶች የከሰዓት በኋላውን የፍርድ ቤቱ የውጭ በር መግቢያ መከፈትን መጠባበቅ የጀመሩት ገና በጊዜ ነበር። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፊታውራሪ አመዴ ለማ እና የወ/ሮ ስንዱ ገብሩ (የክብር ዶ/ር) የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

ፊታውራሪ አመዴ ለማ Fitawrari Amede Lemaየአንጋፋው አርቲስት ጥላሁን ገሠሠን (የክብር ዶክተር) የቀብር ሥነሥርዓት ሐሙስ ይፈጸማል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. April 22, 2009)፦ በአንደበተ ርዕቱነታቸው እና በሀገር ሽማግሌነታቸው የሚታወቁት የፊታውራሪ አመዴ ለማ የቀብር ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት ኮልፌ በሚገኘው የእስላም መስጅድ ተፈጸመ። በተያያዘም እናት አርበኛ፣ የመጀመሪያዋ የሴት የፓርላማ አባልና የደራሲ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ (የክብር ዶክተር) የቀብር ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በአርበኞች የቀብር ቦታ ተፈጽሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፊታውራሪ አመዴ ለማና የመጀመሪያዋ የሴት ፓርላማ አባል ሕይወታቸው አለፈ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 13 ቀን 2001 ዓ.ም. April 21, 2009)፦ በአጼ ኃይለሥላሴ የሥልጣን ዘመን የፓርላማ አባል፣ በሀገር ሸምግሌዎች ህብረት ውስጥ ተካትተው የቅንጅት አመራሮችን ለማስፈታት በተደረገው ጥረት ተሳትፎ የነበራቸው የ89 ዓመቱ ታዋቂው ነጋዴ ፊታውራሪ አመዴ ለማ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 13 ቀን 2001 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙዚቃው ንጉሥ አስክሬን ከመስቀል አደባባይ እንዲነሳ ተወሰነ

(ልዩ ዘገባ)

Artist Tilahun Gessese (Photo, Wikipidia)

- ከአስራ ስድስት ዓመት በኋላ፣ አንገቱ በታረደበት በዚያች ዕለት አረፈ

- የቀብር ሥነሥርዓቱ ሐሙስ በዘጠኝ ሰዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. April 20, 2009)፦ ሁሉም በአንድ ድምፅ “የሙዚቃው ንጉሥ” በማለት የሚያወድሱት የአንጋፋው ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ሞት በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል። ቤተሰቦቹ፣ ዘመድ ወዳጆቹ፣ የሞያ አጋሮቹ፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያንና አድናቂዎቹ በቤቱ እየተገኙ ኀዘናቸውን እየገጹ ነው። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙዚቃው ንጉሥ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

Artist Tilahun GesseseEthiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. April 20, 2009)፦ የሙዚቃው ንጉሥ አንጋፋው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ (የክብር ዶክተር) ከሁለት ቀናት በፊት ከነበረበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 12 ቀን 2001 ዓ.ም. ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

 
ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢየሱስ ክርስቶስና የማሪያም ምስሎች በሆሳዕና ታዩ ተባለ

Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. April 19, 2009)፦ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ከምትገኘው ከሆሳዕና ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፤ በመኪና አንድ ሰዓት በእግር ሦስት ሰዓት ከተጓዙ በኋላ በምትገኘው “ቡሽና” በተባለች ገጠር ቀበሌ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስና የቅድስተ ማሪያም ምስሎች በሁለት ዛፎች ላይ ታዩ ተባለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...