ያልተሳካው ሚሌኒየም

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2001 ዓ.ም. October 19, 2008)፦ የኢትዮጵያን ሚሌኒየምን ለማክበር በከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብስብ የተቋቋመው ብሔራዊ ሚሌኒየም ም/ቤት፣ ትናንት ቅዳሜ ጥቅምት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. ያለፈውን የሥራ ውጤቱን ገምግሞ በይፋ ተዘግቷል። በዚሁ በሼራተን ሆቴል በተካሄደው ሥነሥርዓት ላይ የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሥዩም በረደድ ጽ/ቤቱ ካቀዳቸው 16 ፕሮጀክቶች ግማሹ ያለመሳካታቸውን በሪፖርታቸው ገልፀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቫንኩቨር ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን እያጨቃጨቀች ነው

ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀምሯል

ውሳኔ በሚቀጥለው ሣምንት ይሰጣል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. October 18, 2008)፦ ከተመሰረተች ከ13 ዓመት በላይ የሆናት የቫንኩቨር ካናዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ በተነሳ አለመግባባት የተጀመረው ክርክር በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ መታየት መጀመሩ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ተቀጠረ

የቴዲ አፍሮ ችሎት ሙሉ ዘገባ

“ማረጋገጫ የተሰጠው በዶክተሯ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ አይደለም። ፖሊስ በሰጠው ላይ ተመስርተን ነው” ኩባዊው ዶ/ር ላስፔርቶ

Teddy Afro

Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 16, 2008)፦ የዕለቱ ችሎት የተቀጠረው ከሰዓት በኋላ በመሆኑ ችሎቱን ለመከታተል የፈለጉ በርካታ ሰዎች፣ ፍርድ ቤቱ የጠዋቱን ሥራ አጠናቆ ሳይዘጋ ግቢው መግባት ጀመሩ። ነገር ግን ፖሊስ የቻለውን ያህል ከግቢው ለማስወጠት የሞከረ ሲሆን፣ በግቢው በመዘዋወፈር ያመለጡ ችሎት ተከታታዮች ከቀኑ 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ሲል ተሠልፈው ከነበሩት ጥቂቶቹ የመግባት ዕድል ሲያገኙ በርካቶች ከውጭ ቀሩ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት የግጥም ምሽት በፖሊስ ለአንድ ሰዓት ታገደ

UDJ party Poem evening, 2008,10,16
ተሳታፊዎችን ፖሊስ አግዷቸው በነበረበት ወቅት 
Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 16, 2008)፦ ዛሬ ማምሻውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አዘጋጅቶት የነበረው የግጥም ምሽት ”ፈቃድ የላችሁም” በሚል በፖሊስ ታግዶ የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ ምክንያት ከታቀደበት ሰዓት ለአንድ ሰዓት ያህል ዘግይቶ ተጀምሯል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦባማ የ106 ዕድሜ ባለፀጋዋን መነኩሲት ድምፅ ያገኛል

Sister Cecilia Gaudette መነኩሲት ሲሲሊያን በቴሌቭዥን መስኮት ሲናገሩ ይመልከቷቸው!  

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. October 14, 2008)፦ ነዋሪነታቸው ሮም የሆኑትና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሲስተር (መነኩሲት) ሲሲሊያ ጋውዴት የ106 ዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ፣ በዘንድሮው የአሜሪካን ምርጫ ድምፃቸውን ለሴናተር ባራክ ኦባማ እንደሚሰጡ ጣሊያን ሀገር ለሚታተም አንድ ጋዜጣ ቃለምልልስ ከሰጡ ወዲህ ታዋቂነትን አተረፉ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን ለዳያስፖራው የመገናኛ ብዙኀን የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት ፫-3 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 13, 2008)፦ ትናንት እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2001 ዓ.ም. ማምሻውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በውጭ ሀገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ። ፓርቲውን በመወከል የተገኙት ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት በዓመታዊ በጀቱ ከኢትዮጵያ ፓርቲዎች የመሪነቱን ሥፍራ ያዘ

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት ፪-2 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 12, 2008)፦ አንድነት ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓመታዊ የበጀት ታሪክ ውስጥ በአንደኝነት ደረጃ ላይ ሊያስቀምጠው የሚችለውን የ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት ለያዝነው 2001 ዓ.ም. መያዙ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...