የውይይቱ መንሥኤ፤ ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
ለውድ ፕሮፌሰር ፍቅሬ፤ ከጌታቸው ኃይሌ
“የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” ብለህ የጻፍከው፣ እውነተኛው የዘር ምንጭ አይደለም ጥሩ ተረት ነው ብየ ምክንያቴን ብሰጥ ቁጣህ ከመጠን አልፎ ስድብ ውስጥ ገባህ። “ተረቴን እንደታሪክ አልቀበል ያልክ ሁሉ ጌታቸው የደረሰበትን አይተህ ተቀጣ” ማለትህ ይመስላል። ውይይታችን በመጽሐፍህ ውስጥ ስላካተትካቸው ሐሳቦች እንጂ፣ አንተንና አንዳንድ አራጋቢዎችን እንደመሰላችሁ፣ ስላንተ ወይም ስለኔ አይደለም። እኔ ማስረጃ ይዤ ተረቶች ናቸው ያልኳቸውን አስተዋፅኦችህን አንድ በአንድ ከነማስረጃዬ ዘርዝሬያለሁ፤ ጉዳያችን ያለው እዚህ ላይ ነው። ለናሙና ያህል ከዘረዘርኳቸው ዓሥራ ሦስት ስሕተቶች ውስጥ የአማራው ሕዝብ አባት የተፀነሰው እባሕር ውስጥ ነው ያልከው ስሕተት ይገኝበታል። ስሕተቶች ያልኳቸውን ስሕተቶች አለመሆናቸውን አንድ ባንድ እንድታስረዳ አንባቢህ ይጠብቃል። እውነተኛ ታሪክ ለመሆናቸው ማስረጃው ስድብና ውሸት አይደለም። መልስ መስጠት ካልቻልክ አፍረህና አርፈህ ዝም በል። ማፈርና መልስ አለመስጠት መብትህ ናቸው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...



”ሶቅራጥስ ፈላስፋ ነው። ሚስቱ ደግሞ ጨቅጫቃ ነች። አንዳንዴ ወይዘሮ ይሉኝታና አቶ ይሉኝታ ቢስ ይጋባሉ። ሶቅራጥስ ሲፈላሰፍ ነው የሚውለው። ትዳርዋን ለምትወድ ሴት ደግሞ ይህ ዓይነቱ አካሄድ የሚጥም ሕይወት አይደለም። የሶቅራጥስ ሚስት ሲበዛ ጨቅጫቃ ነበረች።



