በአዲስ አበባ ቦንብ ፈንድቶ አንድ ግለሰብ ላይ ጉዳት ደረሰ

የአዲስ አበባ ታክሲዎች

የሕገወጡ ሕወሓት ቡድን ተላላኪዎች በመዲናዋ የጥፋት ተግባር ለመፈጸም ያዛጋጇቸው የጦር መሣሪዎች ተይዘዋል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 11, 2020)፦ በአዲስ አበባ አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ጠዋት ቦምብ ፈንድቶ በአንድ ግለሰብ ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕወሕት ታጣቂዎቹን የኤርትራ መከላከያ መለዮ በማልበስ “ኤርትራ ወራናለች” እያለ ነው

M. Gen. Mohammed Tessema

መለዮውን ያመረተው በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 11, 2020)፦ ሕወሓት የኤርትራ መከላከያ ሠራዊትን መለዮ በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በማምረትና ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ፤ “ኤርትራ ወራናለች” በማለት ሕዝቡን እያደናገረ መኾኑን የመከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ዛሬ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕግ እስኪከበር የአየር ጥቃቱ ያለከልካይ እንደሚቀጥል የአየር ኃይል አዛዥ አስታወቁ

M. Gen. Yilma Merdassa

የጁንታው እስትንፋስ ከጥቅም ውጭ መኾኑ ተገለጸ

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 11, 2020)፦ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ምርጥ ዒላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉንና “ጁንታው ለሕግ እስኪቀርብ ድረስ ጥቃታችንን እንቀጥላለን” ሲሉ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመቀሌውን ጁንታ ተገቢውን ቅጣት ሳያገኝ ለአፍታም አናርፍም አሉ

PM Abiy Ahmed

ድርድር ብሎ ነገር እንደማይታሰብ አረጋገጡ

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 10, 2020)፦ ስግብግቡንና አረመኔውን የመቀሌ ጁንታ ለፍትሕ ቀርቦ ተገቢውን ቅጣት ሳያገኝ ለአፍታም ቢኾን አናርፍም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ከጁንታው ጋር ምንም ዐይነት ድርድር እንደማይታሰብ አሳውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መከላከያ ሠራዊቱ በሑመራ መስመር በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠሩ ተገለጸ

Gen. Mohammed Tesema and Gen. Berhanu Jula

“በከሃዲው ሕወሓት እጅ ያሉ ከባድ መሣሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ወድመዋል” ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ የመከላከያ ሠራዊት የሑመራ ሱዳን መንገድን ጨምሮ ማይዳሊ፣ ደንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሑመራ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠሩንና በምዕራብ ግንባር እያደረገ ያለውን ጥቃት መቀጠሉን የመከላከያ ኢንዶክትሬሽን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ክልል የባንክ ቅርንጫፎች እየተዘረፉ መኾኑ ተገለጸ

National Bank of Ethiopia (NBE), left and TPLF, right

ብሔራዊ ባንክ ቅርንጫፎቹ ተዘግተው ይቆዩ ብሏል

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ በሕወሓት ውስጥ ያለው ቡድን በክልሉ በሚገኙ ባንኮች ላይ ዘረፋ እየፈጸመ መኾኑንና አሁን ባለው ሁኔታ በትግራይ ክልል ያሉ የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ስለማይችሉ ተዘግተው እንዲቆዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሹመት ሰጡ

አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ ደመቀ መኮንን

አቶ ደመቀ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ደርበው ያዙ
የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹሙና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተነስተዋል
ሌ/ጄኔራል አበባው ምክትል ኤታማዦር ሹም ኾነዋል
የደኅንነትና የፌዴራል ፖሊስ በአዲስ አበባ አመራሮች እንዲመሩ ተደርጓል

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቁልፍ በሚባሉ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሹም ሽር አካሔዱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕወሓት አዲስ አበባን ለማወክ ያዘጋጃቸው 355 የጦር መሥሪያዎች ተያዙ

ሕገወጥ የጦር መሣሪዎያዎች

162 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል
ከሱዳን በገዳሪፍ በኩል ሊገባ የነበረ 95 ሺህ ጥይት ከነግለሰቦቹ ተያዘ

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕወሓት ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው የጦር መሣሪዎያዎችና ተልዕኮውን ለማስፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት (እሁድ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም.) ብቻ በአዲስ አበባ ከ355 በላይ የጦር መሣሪያዎች ተይዘዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከአማራ ርዕሰ መስተዳድርነት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለቀው በአዲስ ተተኩ

አቶ አገኘው ተሻገር እና አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲሱ ተሿሚ አቶ አገኘው ተሻገር ናቸው

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመኾን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኃላፊነታቸውን ለቅቀው አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ተመረጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሁለት የኤፈርት ሕንጻዎች በጸጥታ ኃይሉ ተከቧል

ኤፈርት

ማንም መግባትና መውጣት እንዳይችል ተከልክሏል

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ አዲስ አበባ በቦሌ መንገድ ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ የሚገኘው የሱር ኮንስትራክሽን ዋና መሥሪያ ቤትና ሜጋ ሕንጻ በመባል የሚታወቁት በኤፈርት ባለቤትነት የሚተዳደሩት ሁለቱ ሕንጻዎች በአሁኑ ወቅት በጸጥታ ኃይሎች መከበባቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!