የወዛደሮች ቀን በዓል በከፍተኛ ድምቀት ወ/ት ብርቱካንን በማሰብ ተከበረ

By Matias Ketema (Sweden)

የዓለም የሠራተኞች ቀን በስዊድን, Mayday in Sweden 2009

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. May 2, 2009)፦ በትናንትናው ዕለት የዓለም የወዛደሮች ቀን (ሜይዴይ) በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በሾሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲና በሠራተኛው ማኅበር በተዘጋጀው የወዛደሮች ቀን በዓል ብዙ ሺህ ሰልፈኛ በተገኘበት ተከብሮ የዋለ ሲሆን፣ የስዊድን የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር ባንኛ ቬድን የወ/ት ብርቱካን እስር እንዳሳሰባቸው ባደረጉት ንግግር ላይ ገልፀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን የምትፈታበት ተስፋ እንዳለ የሀገር ሽማግሌዎቹ ገለጹ

Prof. Ephraim Issac ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅ Ethiopia Zare (አርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 1, 2009)፦ የሚመራው የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በታሰረች በአራት ወር ከአራት ቀናቸው ዛሬ ማምሻውን ከ10፡10 ሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ በሸራተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ። በመግለጫቸው ላይ የሽምግልና ዝርዝር ሂደቱን ለመግለጽ ፈቃደኞች ያልነበሩ ሲሆን፤ ወ/ት ብርቱካን የምትፈታበት ተስፋ እንዳለ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቫንኩቨር ቅ/ማርያም ክርክር ተጠናቀቀ

የዳኛ ውሳኔ ይጠበቃል

Ethiopia Zare (አርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 1, 2009)፦ ከሁለት ዓመት በላይ የወሰደው የቫንኩቨር ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ውዝግብ በተለያየ ጊዜ በተደረጉና ሦስት ሣምንታትን በወሰደው ችሎት ትላንት ጠበቆች ባቀረቡት የማጠቃለያ ሃሳብ መጠናቀቁ ታወቀ። ዳኛው ውሳኔያቸውን እስኪሰጡ ከሳሽና ተከሳሽ ወገኖች በትዕግስት እንዲጠበቁ ጠይቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የግንቦት 7 ዓላማ መፈንቅለ መንግሥት ማካሄድ ሳይሆን ባለሥልጣኖችን መግደል ነበር” አቶ በረከት ስምዖን

Ato Bereket Semeon, አቶ በረከት ስምዖንEthiopia Zare (አርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 1, 2009)፦ “የግንቦት 7 ንቅናቄ ዓላማ መፈንቅለ መንግሥት ማካሄድ ሳይሆን ባለሥልጣናቶችን መግደል ነበር” ሲሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምዖን በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ታምራት ታረቀኝ ከአንድነት ፓርቲ ታገዱ

Ethiopia Zare (አርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 1, 2009)፦ በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ታሪክ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ጉልህ ስፍራ ያላቸውና፣ ከቅንጅት አመራሮች ጋር ለ21 ወራት ታስረው የተፈቱት የአሁኑ የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ታምራት ታረቀኝ በብዕር ስም በጋዜጣ ጽፈው ባወጡት ጽሑፍ ፖርቲውን አደጋ ላይ ጥለዋል በሚል ዛሬ ጠዋት ከአንድነት ፓርቲ ለአንድ ወር ታገዱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሮፌሠር ኤፍሬም ከወ/ት ብርቱካን እስር በኋላ የመጀመሪያውን መግለጫ በጽሑፍ ሰጡ

Prof. Ephraim Issac ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅመግለጫው ስለይቅርታው ሂደት ዝርዝር የለውም

Ethiopia Zare (አርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 1, 2009)፦ ከወ/ት ብርቱካን መታሰር በኋላ ድምፁን አጥፍቶ የነበረው የሀገር ሽማግሌዎች ሕብረት መሪ ፕሮፌሠር ኤፍሬም ይስኃቅ ኢትዮጵያ በመሆናቸው በዛሬው ዕለት በ10 ሰዓት በሸራተን ሆቴል መግለጫ እንደሚሰጡ ለጋዜጠኞች ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የቅንጅት አመራሮች የተፈቱበትን የይቅርታ ሂደት በሚገባ የማያብራራ መግለጫ ትናንት ኀሙስ ሚያዝያ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ለተወሰኑ ጋዜጠኞች በጽሑፍ ሰጥተዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አባል በግንቦት ሰባት ስም ተጠርጥው ከታሰሩት ውስጥ አንዱ ናቸው

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የቅርብ ዘመድ ከአቶ ነጋ ቦንገር ቤት ተይዘው ታስረዋል

Ethiopia Zare (አርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 1, 2009)፦ ባለፈው ሣምንት የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ናቸው ብሎ ካሰራቸው 35 ሰዎች ውስጥ፤ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መስራችና የምክር ቤት አባል አቶ መላኩ ተፈራ፣ በኢህአዴግ የትጥቅ ትግል ዘመን ስመጥር የጦር መሪ ብርጋዴር ጄኔራል ተረፈ ማሞ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አባት የ80 ዓመቱ አቶ ጽጌ ኃብተማርያም እና የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የቅርብ ዘመድ አቶ ጌቱ ወርቁ ይገኙበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...