የሙዚቃው ንጉሥ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
|
|
Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. April 19, 2009)፦ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ከምትገኘው ከሆሳዕና ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፤ በመኪና አንድ ሰዓት በእግር ሦስት ሰዓት ከተጓዙ በኋላ በምትገኘው “ቡሽና” በተባለች ገጠር ቀበሌ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስና የቅድስተ ማሪያም ምስሎች በሁለት ዛፎች ላይ ታዩ ተባለ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከሣምንት በኋላ ጠይቁን ተብለዋል
Ethiopia Zare (ዓርብ ሚያዝያ 9 ቀን 2001 ዓ.ም. April 17, 2009)፦ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ወቅት ተቀጥረው ሥራ የጀመሩት መለስካቸው አምሃ እና እስክንድር ፍሬው የተባሉት የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጣቸውንና መዘገብ የሚያስችላቸውን ፈቃድ መቀማታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ። መንግሥት በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዘገባ አለመደሰቱን ከመግለጽ ውጭ የተባሉት ነገር የለም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. April 16, 2009)፦ ከምርጫ 97 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈቀደውን ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የአንድነት አመራሮች ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ ነበር በአንድነት ቢሮ መሰባሰብ የጀመሩት።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. April 16, 2009)፦ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ዘፈኖች በኤግዝቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው "የአዲስ ፋሲካ የንግድ ትርዒት" ዝግጅት ላይ እንዳይዘፈኑ ተከለከለ።
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. April 16, 2009)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አያሌ የፌደራሉ መንግሥት እና የመዲናይቱ ፖሊስ አባላት ከደምወዝ ክፍያ ማነስ ጋር በተያያዘ ሥርዓቱን እያማረሩ መሆናቸው ታወቀ። ከመካከላቸውም "በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ ያስፈልጋል፣ በወገናችን እየተጠላን መኖሩ ታክቶናል፣ የእኛም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ሕይወት በቃላት ድርደራ ካልሆነ በቀር በተግባር አልተለወጠም" በማለት መንግሥቱን የሚያማርሩ እንዳሉም ምንጮች አረጋግጠዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...'ታጋይን በማሰር ትግልን ማቆም አይቻልም!' ሰልፈኞች
ህዝብ በየቦታው ቆሞ እየተከታተለ ነው
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. April 16, 2009)፦ ዛሬ ጠዋት የጀመረው የአንድነት ፓርቲ ሠላማዊ ሰልፍ ብዛት ያላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በቅርበት እየተከታተሉት ከመሆኑም በላይ በአሁኑ ሰዓት በቤተመንግሥት አካባቢ በከፍተኛ ድምፅ መፈክሮችን እያሰሙ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. April 16, 2009)፦ በእስር ላይ ያሉት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ብቻዬን በመታሰሬ የሰብዓዊ ክብሬ ተገፏል ብለው ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማድረጉን ትናንት መዘገባችን አይዘነጋም። ማረሚያ ቤቱ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይገናኙ አድርጎ ብቻቸውን የማሰር ሥልጣን አለው ሲል የፌደራል የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት ዘጠነኛ ችሎት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፤ ለሁለተኛው ክስ "በቅርብ ጓደኞቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም በሐኪማቸው፣ የሕግ ባለሙያ እና በኃይማኖት አባት የመጎብኘት መብት ባለቤት መሆናቸው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 እና በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/99 አንቀጽ 13 ላይ ስለተረጋገጠ ተከሳሽ ለሌሎች እስረኞች ይህንን በሚያከብርላቸው መልክ የከሳሽንም እነዚህ መብቶችን እንዲያከብርና በከሳሽ ላይ የጣለው ክልከላ እንዲነሳ ተወስኗል" በማለት መዝገቡን ዘግቷል። የውሳኔውን ሙሉ ቃል እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ማረሚያ ቤቱ እስረኛዋን ለብቻዋ ማሰር ይችላል ተብሏል
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. April 15, 2009)፦ ለሦስት ወራት ከ17 ቀን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በታጣቂዎች ታፍና ወደ ቃሊቲ እስር ቤት የተጣለችው ብቸኛዋ የሴት የፖለቲካ መሪ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በጠበቃዋ፣ በሐኪሟ፣ በኃይማኖት አባቷ፣ በቤተሰቦቿ፣ በወዳጅ ዘመዶቿና በጓደኞቿ የመጎባኘት መብቷ የተረጋገጠ መሆኑን ዛሬ በአዲስ አበባ የተሰየመው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሰልፉ ነገ ጠዋት ይደረጋል
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 7 ቀን 2001 ዓ.ም. April 15, 2009)፦ የዓለም ፓርላማ አባላቶች ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል በሚል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የወ/ት ብርቱካንን እስር በመቃወም ያዘጋጀው የሠላማዊ ሰልፍ ተፈቅዶ፤ ነገ ሚያዝያ 8 ቀን 2001 ዓ.ም. (April 16, 2009 እ.ኤ.አ.) ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን አረጋገጡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...