በማትያስ ከተማ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2002 ዓ.ም. May 3, 2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የዓለም ወዛደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ። በዚህ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲና የሠራተኛው ማኅበር ባዘጋጁት በዓል ላይ ብዙ ሺህ ህዝብ የተገኘ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያንም የሰልፉ ተካፋይ ነበሩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም. April 30, 2010)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቤት መኪና በመገጣጠም የሚታወቀውና ”ሆላንድ ካር” የተሰኘው ኃ.የተ.ኩባንያ፤ ሁለት አይነት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። አንደኛው 130 ሰዎች የሚጭን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ባለአንድ ፎቅና 240 ሰዎችን የሚጭን መሆኑን አስታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
እነኢ/ር ግዛቸው የፓርቲውን የምስክር ወረቀት፣ ጽ/ቤቱን፣ ማሕተሙን፣ ሰነዶችና ንብረቶች እንዲያስረክቡ ተጠየቁ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም. April 27, 2010)፦ እነፕ/ር መስፍን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን (አንድነትን) ሕጋዊነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ ጽሕፈት ቤቱን፣ ማሕተሙን፣ ሰነዶችና ንብረቶችን እንዲያስረክቧቸው፤ ማሕተሙን እንዳይጠቀሙና እንቅስቃሴአቸውን እንዲያቆሙ ትናንት ለኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው የፃፉላቸውን ደብዳቤ አልቀበልም ማለታቸውን አስመልክቶ፤ በዛሬው ዕለት ”የአንድነትን ሕልውና የመታደግ ጥረታችንን ሕገወጥነት አይገታውም” በሚል መግለጫ አወጡ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም. April 26, 2010)፦ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ፤ የመድረኩ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ”ሕገ መንግሥቱን የሚፃረርና ኹከት የመፍጠር አዝማሚያ ያለው ንግግር አድርገዋል” በማለት ዛሬ ማምሻውን መግለጫ አወጣባቸው። መግለጫው ”ሕግ የጣሰ ነው” ያለውን የፕ/ሩን ንግግርም ሆነ ወደፊት በሚደረጉ ተመሳሳይ ንግግሮችና መግለጫዎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን ይላል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም. April 26, 2010)፦ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በዕጩዎቹና በአባላቶቹ ላይ ከፍተኛ ወከባና እንግልት እየተፈጸመ መሆኑን ገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም. April 26, 2010)፦ ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. የቀረው ጊዜ በቀናት የሚቆጠሩ ሲሆን፤ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ ቦታዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳና ሌሎችም ኢትዮጵያዊያን የኅሊና እስረኞች የከፈሉትና በመክፈል ላይ የሚገኙት መስዋዕትነት በገንዘብ ሊተመንና ከቶም ሊካካስ የማይችል መሆኑ ተገለጠ። ይህ የተገለጠው፣ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 6 ቀን 2010 በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት “ድጋፍና አክብሮት ለኅሊና እስረኞች” በሚል መርኅ በሂዩስተን ከተማ የተከናወነው በኢትዮጵያ የሚገኙ የኅሊና እስረኞች ማሰቢያና ድጋፍ ማሳያ ሥነሥርዓትን ያቀጋጀው ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ ላይ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 13 ቀን 2002 ዓ.ም. April 21, 2010)፦ በምክትል ሊቀመንበሩ ኢንጂንየር ግዛቸው የሚመራው አንድነት ”የፓርቲ አፍራሾች” ባላቸው በእነ ፕሮፌሠር መስፍን ላይ መግለጫ አወጣ። ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 13 ቀን 2002 ዓ.ም. April 21, 2010)፦ እሁድ ሚያዝያ 10 ቀን 2002 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ባልደረቦች የሆኑ ትራፊኮችና ሌሎች የፖሊስ አባላት ለሥልጠና ወደ ሰንዳፋ ማምራታቸው ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...