ኢሳት “እሳት” ተባለ፤ የተመልካቾቹ ቁጥር እያሻቀበ ነው

“ኢሳት ሁለት ወር ቀደም ቢል ኖሮ ምርጫው የኛ ይሆን ነበር” አስተያየት ሰጪዎች

በተክለሚካኤል አበበ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የተከታታዮቹ ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ከምርጫው በፊት ቢጀመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርግ እንደነበር ተገለጸ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአባ ጳውሎስ ወኪል አባ ማትያስ ንጉሴ ወደ ቫንኩቨር ሊያቀኑ ነው

Aba Matiasበቫንኩቨር ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. May 20, 2010)፦ በቶሮንቶ ካናዳ የአባ ጳውሎስ ቀኝ እጅ የሆኑት አባ ማትያስ ንጉሴ ደስታ በዚህ በያዝነው ሣምንት (ሜይ 23-24) በህሆተ ሰማይ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ጋባዥነት ወደ ቫንኩቨር እንደሚመጡና ቤተክርስቲያኗ ወደ አባ ጳውሎስ ስር እንድትገባ ተግተው ሲሰሩ የነበሩት ሰዎችም አባ ማትያስን ለመቀበል ሽር ጉድ እያሉ እንደሆነ ምንጮች ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በተንቤን የአቶ ስየ ቅስቀሳ ችግር ገጥሞታል

Ato Seye AbrhaW/o Aregash Adaneወ/ሮ አረጋሽ በአድዋ የጠሩት ስብሰባ ብጥብጥ አስነሳ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ግንቦት 12 ቀን 2002 ዓ.ም. May 20, 2010)፦ ከሦስት ቀናት በኋላ ከፍተኛ የ‘ምርጫ’ ፉክክር ይካሄድበታል ተብሎ በሚጠበቀው በትግራይ ክልል በተምቤን እና አድዋ ወረዳዎች አቶ ስየ አብርሃ እና ወ/ሮ አረጋሽ በሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ከፍተኛ ወከባ እየገጠማቸው መሆኑን ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረክ በመስቀል አደባባይ የጠራው ስብሰባ ተከለከለ

በደብረዘይትና በአዲስ አበባ የመጨረሻ ቅስቀሳውን ያካሂዳል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 7 ቀን 2002 ዓ.ም. May 15, 2010)፦ መድረክ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 7 ቀን 2002 ዓ.ም. (ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም.ትን በማሰብ) በመስቀል አደባባይ ሊጠራው ያሰበው ህዝባዊ ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የመድረክ አባላት አንድ ፖሊስ ገደሉብኝ” የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. May 9, 2010)፦ በዛሬው ዕለት የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን በመጥቀስ፤ ”በመድረክ ፓርቲ የተደራጁ ሦስት ግለሰቦች አንድ ፖሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ወግተው ገደሉ” በማለት መዘገባቸው ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አስረዳ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወዛደሮች ቀን ተከበረ

በማትያስ ከተማ

  • ሞና ሳሊን ብርቱካን ሚደቅሳ እንድትፈታ ጠየቁ
  • የኢትዮጵያን መንግሥት ሥርዓት የለሽነት አጋለጡ

May day 2010, Stockholm, Sweden

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2002 ዓ.ም. May 3, 2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የዓለም ወዛደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ። በዚህ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲና የሠራተኛው ማኅበር ባዘጋጁት በዓል ላይ ብዙ ሺህ ህዝብ የተገኘ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያንም የሰልፉ ተካፋይ ነበሩ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ውስጥ አውቶቡስ ሊሠራ ነው

Holand Car PLC's Abay carEthiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም. April 30, 2010)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቤት መኪና በመገጣጠም የሚታወቀውና ”ሆላንድ ካር” የተሰኘው ኃ.የተ.ኩባንያ፤ ሁለት አይነት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። አንደኛው 130 ሰዎች የሚጭን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ባለአንድ ፎቅና 240 ሰዎችን የሚጭን መሆኑን አስታውቋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...