የዲ.ኤች. ገዳ ባለቤት በድንገት አረፉ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 2 ቀን 2001 ዓ.ም. January 10, 2009)፦ በተለያዩ የንግድ ዘርፍ በመሰማራት የታወቁትና የዲ.ኤች. ገዳ ባለቤት የሆኑት አቶ ደጉማ ሁንዴ በድንገት ትናንት (ዓርብ ጥር 1 ቀን) ከዚህ ዓለም መለየታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 2 ቀን 2001 ዓ.ም. January 10, 2009)፦ በተለያዩ የንግድ ዘርፍ በመሰማራት የታወቁትና የዲ.ኤች. ገዳ ባለቤት የሆኑት አቶ ደጉማ ሁንዴ በድንገት ትናንት (ዓርብ ጥር 1 ቀን) ከዚህ ዓለም መለየታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ ጥር 1 ቀን 2001 ዓ.ም. January 09, 2009)፦ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጋዜጦች የሚታተሙበት ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት፣ ወደ 12 በመቶ የሚሆን የዋጋ ጭማሪ አደረገ። በርካታ አሣታሚዎች ጭማሪው ፕሬሶችን “ወደ ጉድጓድ የሚከት ነው፣ ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል” ብለዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳና ቴዲ አፍሮ በጉልህ ይጠቀሳሉ
በሲያትል ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. January 06, 2009)፦ ያለአግብብ የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ታላቅ ዓለማቀፍ ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና በተለይ እውቁን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮንና የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ድርጅት መሪ የሆነችውን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሁኔታ በጉልህ የሚያሳይ ዓለማቀፍ የአዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቋመ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. January 05, 2009)፦ ሰኞ ዕለት በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳንና የቴዎድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮ) አለአግባብ መታሰር፤ እየተፈጸመ ያለውንም ግፍና በደል፤ እንዲሁም የዲሞክራሲ መታፈንን፤ በመቃወም በስቶክሆልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት በራፍ ተገኝተው ቁጣቸውን ገለጹ።
የሕትመት ዋጋን በመጨመር ነፃው ፕሬስ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ነው
Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2001 ዓ.ም. January 05, 2009)፦ በመንግሥት የሚተዳደረው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ከጥር አንድ ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ በጋዜጦች ላይ የሕትመት ዋጋ የሚጨምር ሲሆን፣ ከምርጫ 97 በኋላ የተቋቋሙት ጥቂት የፕሬስ ውጤቶች ከገበያ እንዲወጡ የሚያደርጋቸው መሆኑ ታወቀ። “ፕሬሱን ለማዳፈን የታለመ ነው” ተብሎ ተተችቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወ/ት ብርቱካንን መጠየቅ አይቻልም፤ እናትና ልጃቸው ብቻ ተፈቀደላቸው
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. January 03, 2009)፦ ቅዳሜ ዕለት ወ/ት ብርቱካንን ቃሊቲ ወሕኒ ቤት ለመጠየቅ የሄዱ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ለረዥም ሰዓታት እንዲጠብቁ ከተደረገ በኋላ ገብተው እንዳይጠይቋቸው ተከለከሉ። የወ/ት ብርቱካን ወላጅ እናትና የአራት ዓመት ሕፃን ልጃቸው ብቻ ለ40 ደቂቃ አገኟቸው። ሕፃንዋ ልጃቸው ከቃሊቲ እስር ቤት ስትወጣ ተንሰቅስቃ አለቀሰች።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. January 02, 2009)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የፖለቲካ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትና የ34 ዓመቷ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከታሰሩበት ያለፈው ሰኞ ታህሳስ 20 ጀምሮ ሁለት በሁለት በሆነ ክፍል ውስጥ ለብቻቸው የታሰሩ ሲሆን፣ ላለፉት አምስት ቀናት በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. January 02, 2009)፦ አዲሱ የዓባይ ድልድይ በተመረቀ በአራት ወሩ በዚህ በያዝነው ሣምንት ለትራፊክ (ለተሽከርካሪዎች) አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ክፍት መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።
በስዊድን የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ሰጪ ማኅበር መግለጫ አወጣ
Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. January 02, 2009)፦ በስዊድን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የድጋፍ ሰጪ ማኅበር የወ/ት ብርቱካንን መታሰር አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ሊቀመንበሯ ካለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን መታሰር አስመልክቶ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ “የብርቱካን ሚደቅሳ እንደገና መታሰር በሀገራችን እየታየ ያለውን የሕግ ጥሰት አጉልቶ ያሳያል፤ ከሕግ በላይ መሆን ይቁም!” በማለት መግለጫ አውጥቷል። በዚሁ መግለጫው የሊቀመንበሯ መታሰር በሳቸው ላይ ሳይሆን በፓርቲው ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል ኮንኖታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...