ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ይቅርታው ተነስቶባቸው ዕድሜ ልክ ታሰሩ

W/t Birtukan MideksaEthiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 20 ቀን 2001 ዓ.ም. December 29, 2008)፦ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በቅንጅት አመራርነታቸው ወቅት ከተከሰሱበትና ከተፈረደባቸው በኋላ በሽምግልና ቢፈቱም፤ ይቅርታው ተነስቶባቸው ቀድሞ የተፈረደባቸው የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈፃሚ እንዲሆን በማለት ገዥው የኢህአዲግ ፓርቲ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንደወረወራቸው የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስረዱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ78 ዓመቱ ፕ/ር መስፍን ተደበደቡ፣ ወ/ት ብርቱካን የደረሰችበት አልታወቀም

Prof. Mesfin WoldemariamW/t Birtukan Mideksaድርጊቱ የተፈጸመው ከፓስተር ዳንኤል ጽ/ቤት ሲወጡ ነው

Ethiopia Zare (ሰኞ ታህሳስ 20 ቀን 2001 ዓ.ም. December 29, 2008)፦ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ወደ 8፡30 ሰዓት አካባቢ ቦሌ ከሚገኘውና ከሽማግሌዎቹ አንዱ ከሆኑት ፓስተር ዳንኤል ጽ/ቤት ለአራት ሰዓታት ቆይተው የወጡት የ78 ዓመቱ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ተደብድበው ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ደግሞ ታስረው ወዴት እንደተወሰዱ ለጊዜው ለማረጋገጥ አልተቻለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምክክር መድረክ ከህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደ

ስድስት ምሁራን የውይይት ጽሑፋቸውን አቅርበዋል

Ethiopia Zare (እሁድ ታህሳስ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. December 28, 2008)፦ መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ (የምክክር መድረክ) ቅዳሜ ዕለት በኢምፔሪያል ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት ዝግጅት ላይ ስድስት ምሁራን የውይይት ጽሑፍ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ቃሌ”- ከወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ

W/t Birtukan Mideksaወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሽምግልናውን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጡት ቃል

ታህሳስ 14 ቀን 2001 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ጽ/ቤት ተገኝቼ ማስጠንቀቂያ ሲነገረኝ እና ያው መልዕክት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲተላለፍ ስመለከት ያደረብኝን ስሜት ለመግለጽ ያዳግተኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮ ይግባን ለዛሬ ወር ተቀጠረ

Teddy Afroበውጭ ሆኖ እንዲከራከር ጠየቀ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. December 27, 2008)፦ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ ሰው በመኪና ገጭቶ በመግደል እና የተገጨን ሰው ባለመርዳት በሚል ለቀረበበት ክስ፣ የተጣለበት የስድስት ዓመት እስር እና የ18 ሺህ ብር ቅጣት ተነስቶ፣ በነፃ እንዲሰናበት ያቀረበው ይግባኝ ለጥር 18 ተቀጠረ። የቀረበው ይግባኝ ውሳኔ እስኪያገኝም ድረስ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነው ውሳኔ ታግዶ በውጭ ሆኖ እንዲከራከር እንዲወሰንለት የሚጠይቀውን አቤቱታ ዓርብ ገቢ አድርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢፌዲሪ ዓርማ የሌለበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ ያሳተሙ ተከሰሱ

የማተማያ ቤቱ ሥራ አስኪያጅም ተከሰዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. December 27, 2008)፦ የቡና ተክል ልማት ድርጅት ለሚሊኒየም ላሳተመው የእንኳን አደረሳችሁ፣ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ ፖስት ካርድ ላይ፣ ከድርጅቱ ስምና ዓርማ ጋር የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለ ዓርማ በመታተሙ፣ ሦስት የድርጅቱ ኃላፊዎችና ፖስት ካርዱን ያሳተመው ማተሚያ ቤት ሥራ አስኪያጅ ክስ ቀረበባቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

38 የሥራ ኃላፊዎችና ግለሰቦች በሙስና ተከሰሱ

ክሱ በሕገወጥ የመኪና ዝውውር በሚል ነው

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. December 27, 2008)፦ የኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጽ/ቤት ዘጠኝ የሥራ ኃላፊዎች፣ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸውን ከ15 በላይ ተሽከርካሪዎች፣ በሕገወጥ መንገድ የተሠሩ ሐሰተኛ የባለቤትነት ደብተር፣ ሠሌዳ ቁጥሮችንና የማዘዋወሪያ ቅፆች መሆናቸውን እያወቁ ተለዋጭ ካርታና ሊብሬ ሰጥተዋል ሲል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቶባቸዋል። በድርጊቱ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊና ተባባሪ ናቸው ባላቸው 29 ተጠርጣሪዎች ላይም ተመሳሳይ ክስ አቅርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ታስረው ተፈቱ

መኢአድ ዋና ፀሐፊውን ከሥራ ማሰናበቱን የጽ/ቤቱ በር ላይ በመለጠፍ አሳወቀ

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. December 26, 2008)፦ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የፓርቲው ልሳን (አንድነት) ጋዜጣ፣ ዋና አዘጋጅ ወይዘሪት መሶበወርቅ ቅጣው ከእስር ተለቀቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነፃው ፕሬስ አሣታሚ ድርጅቶች ለፍ/ቤት ተቃውሟቸውን አቀረቡ

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. December 26, 2008)፦ “ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለመናድ” በሚል፣ በእነ ኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል የክስ መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት፤ “ሰርካለም አሣታሚ ድርጅት” 120 ሺህ ብር፣ “ሲሳይ የሕትመትና የማስታወቂያ ድርጅት” 100 ሺህ ብር የተጣለባቸውን ቅጣት እንዲከፍሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ለቀረበባቸው አፈፃፀም ክስ፣ ጉዳዩ በይቅርታ የተቋጨ በመሆኑ ልንጠየቅ አይገባም ሲሉ መከራከሪያቸውን ለፍርድ ቤት አቀረቡ። ፍርድ ቤቱ መከራከሪያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ደርሶት ለሰኞ መልስ እንዲሰጥበት አዟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ደህንነት አደጋ ላይ ነው

W/t Birtukan Mideksaበቀን አራት መኪኖች ይከታተሏቸዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. December 26, 2008)፦ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑንና በየቀኑ አራት መኪኖች እንደሚከታተሏቸው የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...