... ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ሦስት) - አያልሰው ደሴ

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ሦስት (ከክፍል ሁለት የቀጠለ)

ከአያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ) አገር ወዳድና ህዝባዊ (ዴሞክራሲያዊ) ኃይሎች፤

ከፍ ሲል በ’ለ’ ስር ለማሳየት እንደተሞከረው ለሀገራችንና ለህዝቧ አዎንታዊ ለውጥን ለማስገኘት በልዩ ልዩ መልክ የሚጋገለውና በጥቅሉ ”ተቃዋሚ ክፍል” የተባለው ወገን ሥልጣን ላይ ካለው ገዥ ክፍል ከኢህአዴግ ጋር የሚኖረውን አንፃራዊ አሰላለፍ በተገቢ መመርመር ያስፈልጋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያን የአማራ ያደረጋት ማነው?

መክብብ ማሞ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ታሪካዊው ‹‹ምርጫ›› በኢትዮጵያ ከተደረገና ህወሃት/ኢህአዴግ ራሱ ጥያቄውን አውጥቶ፣ ፈተናውን ካረመና በውጤቱ A+ ማግኘቱን ከነገረን ወዲህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች መንደር ‹‹የአሁኑ ጊዜ ተከፋፍለን የምንጨቃጨቅበት ሳይሆን የአንድነት ነው›› በማለት ተባብሮ የመሥራት ጥያቄና ሃሳብ ሲቀርብ ሰንብቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጊዮርጊሱ ግርግር - መልካም አዲስ ዓመት!

ምድረ ቺካጎ (ግርማ ካሣ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ነሐሴ 27 ቀን 2002 ዓ.ም.

አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ ነው። ሰዎች በአንድ ቦታ ተከማችተዋል። ግርግር ነገር ይታያል። በመንገድ የሚያልፉ አንድ አባት በመኪና ውስጥ አብረዋቸው ያሉትን «ምንድን ነው የተፈጠረው?» ይሉና ይጠይቃሉ። ሹፌራቸው መኪናውን ቀስ አድርጎ እንዲያቆም ያዛሉ። ከሹፌሩ ሌላ አብሯቸው መኪናው ውስጥ የሚገኝ አንድ ወጣት ከመኪናው ወርዶ፣ ነገሩ ምን እንደሆነ አጣርቶ እንዲመጣ ይልካሉ። ወጣቱ፣ ፈጥኖ ብዙ ሰዎች ወደ ተሰበሰቡበት ያመራል። እየሆነ የየነበረውን ተመልክቶ ይመለሳል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በውሸት ደዌ ለምትሰቃዩ - እነሆ እውነቱን! የአፍሪካም ጭራ ነን (ሲሳይ አጌና)

ሲሳይ አጌና - ከአዲስ አበባ

ከአምስት አመት በፊት 1997 ኢትዩጵያ ዲሞክራሲን አማጠች፤ የተስፋ ብርሃንም ተንቦገቦገ፤ ኢትዮጵያ ሚያዚያ 30 የጀመራትን ምጥ ግንቦት 7/97 ተገላገለች። ዲሞክራሲ ተወለደ። ግንቦት 7 አመሻሹ ላይ ህጻኑ ዲሞክራሲ ህመም ጀመረው፤ በማግስቱም ህመሙ ጸናበት፤ ህጻኑ አንዴ እየተሻለው ሌላ ጊዜ ደግሞ እየበረታበት ግንቦት 29 ሀወመሙ አጣደፈው፤ ግምቦት 30 ይበልጥ በረታበት፤ ሰኔ አንድ ቀን ነፍሱ አልወጣ አለች እንጂ በድን ሆነ። አዎ ህጻኑ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በ “ኮማ” (ሰመመን) ውስጥ ለአራት ወራት ያህል ቆይቶ ጥቅምት 22/98 ዓ.ም አሸለበ። ሁሉም ነገር ወደ ኋላ ተመለሰ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአምስተርዳም እንዳየነው፤ የተሳካ የስፖርት ፌስቲቫል፤ ያልተሳካ የባህል ትእይንት

ልጅ ተክሌ ከአምስተርዳም

ስፖርትና ፖለቲካ፦ ከቫንኩቨር እስከ አምስተርዳም

መቼም ሰዊትዘርላንድና ኮለን ተጫውተው ሰዊትዘርላንድ ዋንጫ በላ። በዝግጅቱም ላይ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው ነበር። ከጣሊያን እስከ ኖርዌይ እስከ እንግሊዝ የመጡ ቡድኖች ተጫውተው … የሚል ጽሁፍ አትጠብቁም። ከዚያም ጠልቀን መሄድ አለብን። ፈርዶብኝ ይሄ ክፉኛ የተጸናወተኝ ሁሉንም ነገር በፖለቲካ መነጽር የማየት በሽታ ጸንቶብኛል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳት በቫንኩቨር የማስታወቂያና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄደ

ቅዳሜ ጁላይ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በምእራብ ካናዳዋ ውብ ከተማ ቫንኩቨር በተካሄደ የኢሳት የማስተዋወቂያና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከሚጠበቀው በላይ ድጋፍ ማግኘታቸውንና የተሳካ ዝግጅት ማድረጋቸውን የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ገለጹ። ሙሉውን አስነብበኝ ...