ጎብላን አጭበርባሪው ጦጣ (አሥራደው)

አሥራደው (ከፈረንሣይ)

ማሳሰቢያ

ከአቤ ጉበኛ መጻሕፍት የአንዱን ርዕስ መዋስ የመረጥኩት፤ ያለንበትን ዘመን ገላጭ ሆኖ በማግኘቴ ነው። ሃቀኛውና ደፋሩ አቤ ጉበኛ፤ በነበረበት ዘመን ለማንም ሳያጎበድድ በሰላ ብዕሩ የሚያስበውን ብሎ ሰው እንደሆነ፤ ሰው የሚያሰኘውን ሥራ ሠርቶ አልፏል። ይህ ፈጣሪ ለጥቂቶች የሚቸረው ተሰጥዖ ነው። እናም ቀናሁበት - መንፈሣሳዊ የታናሽ ወንድምነት ቅናት! ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከዝንብ ማር አንጠብቅም

ሚሊዮን ጎሣዬ (ከኦስሎ - ኖርዌይ)

አይሆንም እንጂ ቢሆንና ዝንብ ማር መስጠት ብትጀምር ከአዲስ አበባ አካባቢዎች እንደ ተክለኃይማኖትና መርካቶ ማርን በብዛት የሚያመርት ይኖራል ብዬ አልገምትም። ለምን? ቢሉ አዲስ አበባ ምን ትላለች እኔም አፍንጫ የለኝም ነው ያለው ጋሽ ስብሃት። እውነታው ግን ዝንብም ማር ሰጥታ አታውቅም፤ ወያኔም ዴሞክራሲያዊ ምርጫን። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የስየ ሀገር

Ato Siye Abrha አቶ ስየ አብርሃጽዮን ግርማ - ከትግራይ

በመኪና ከአቢአዲ የአንድ ሰዓት፤ በእግር ደግሞ ለሦስት ሰዓት የሚያስጉዘውን፣ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማ፣ ጠመዝማዛ እና ድንጋያማ መንገድ አቆራርጠን ዳገት ላይ ከሚገኝ አንድ ቤት ደረስን - ቅዳሜ ግንቦት 14 ቀን 2002 ዓ.ም.። የቤቱ ብረት በር ተከፈተልን እና ወደ ውስጥ ዘለቅን። በድንጋይ የተሠራው ቤት ሰፊ ሳሎን አለው። አነስ አነስ ያሉ አራት መኝታ ክፍሎችንም ይዟል። የቤት ዕቃዎቹ አርጅተዋል፤ ሰፊው ግቢ አካባቢው ላይ በስፋት በሚገኘው ቀይ ድንጋይ ታጥሯል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በምርጫ ዋዜማ - ከ“ተንቤን” እስከ ”ዓዲሓ”

ጽዮን ግርማ - ከተንቤን

በአገሪቱ ቀደም ሲል የተከናወኑት ሦስት ምርጫዎች፤ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ፓርቲ ሌላ እንዲመርጥ ዕድል ሳይሰጡት አልፈዋል። ህወሓት በትግራይ ብቻውን ይወዳደራል፤ ብቻውን ያሸንፋል። የዘንድሮ ምርጫ ግን ይህን ልማድ ገፎ የጣለው ይመስላል፤ ዐረና መድረክ እና አንድነት መድረክ ዕጩዎቻቸውን ወደ ትግራይ ልከዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫ 2002 እና ቀጣዩ የትግል አቅጣጫ (ክርስቲያን)

ክርስቲያን ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

የምርጫ 2002 ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ተጠናቀቀ። ከእባብ ዕንቁላል የእርግብ ጫጩት የጠበቁ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተደናግጠው የሚሉትን አጥተው ዝምታን መርጠዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በሠላማዊ መንገድ ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን ለማወቅ ምርጫ 1997 ወይም ምርጫ 2002 አስፈላጊዎች አልነበሩም (ይህ የኔ የግል አስተሳሰብ ነው)። የአቶ መለስ ዜናዊን አምባገነንነት እስከ አሁን ያልገባው ካለ አውቆ የተኛ መሆን አለበት። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሠላማዊ ትግል ፈተና (መርስኤ ኪዳን)

መርስኤ ኪዳን

ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. የተካሄደው ምርጫ ማንም ባልገመተው መልኩ በኢህአዲግ ሙሉ በሙሉ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። ይህ ውጤት ለተለያዩ አካሎች የተለያየ ትርጉም ይኖረዋል። በውጭ ሀገር ሆነው ”ሠላማዊ ትግል ዋጋ የለውም፤ ኢህአዲግን በተገኘው መንገድ ሁሉ በማጥቃት መደምሰስ ያስፈልጋል” ለሚሉ ለዚህ አቋማቸው ማረጋገጫ እንደሆነ አድርገው ይወስዱታል። በሀገር ውስጥ በሠላማዊ መንገድ ዓላማቸውን ለማሳካት ሲጥሩ ለቆዩት ደግሞ በሠላማዊ ትግልና በአመፅ መካከል አንዱን እንዲመርጡ የሚያስገድድ ሁኔታ ፈጥሯል። የዚህ ጽሑፌ ትኩረት የሚሆነው እነዚህ በሠላማዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፓርቲዎች የገጠማቸውን ፈተና ለመዳሰስና በበኩሌ ያዋጣል የሚለውን ለመጠቆም ነው። ወደዋናው ጉዳይ ከማምራቴ በፊት ግን፤ ይህ ያልተጠበቀ ውጤት እንዴት ተከሰተ የሚለውን ለማየት እሞክራለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሁን ምን እናድርግ? (ይሄይስ አዕምሮ)

ይሄይስ አዕምሮ

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ጣቢያ፦

በቅድሚያ እንኳን ለ”ምርጫ 2002 በሠላም አደረሳችሁ!” ብዬ እንዳልጀምር ራሴን አከላከልኩትና፤ እንግዲያውስ ” እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ለተቀበለውና እንዳይኑ ብሌን በስስት ለሚያየው የኢሳት ወይም የእሳት ቴሌቭዥን ሥርጭት መጀመር በሠላም አደረሳችሁ!” ማለትን ወደድኩ። የሚያግባባን ይመስለኛል። በዚያውም እናንተን ጨምሮ ብዙ ሰው ከማስቀየም እድናለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከምርጫው በስተጀርባ - አንዳንድ ነጥቦች (ተስፋዬ ገብረአብ)

ተስፋዬ ገብረአብ

(አንዲት ቁራጭ “ወግ” ይዣለሁና እንደ መለስ ዜናዊ ቅንድባችሁን አሳምራችሁአንብቡኝ። “ጠቢቡ ሰለሞን” ለመሪያችን እንዳቀነቀነለት፣ “ውበት ቅንድቡ ላይ የፈሰሰለት - እውቀት ወደ አንጎሉ የዘለቀለት!” ተባለ። አልን! አስባልን! ይባላል! በምርጫው ዋዜማ አንድ ጓደኛዬ ዘንድ ቤቱ ሄጄ ሳለ፣ ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ቅንድቡ ያማረው” (መክብብ ማሞ)

መክብብ ማሞ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ሳፓርሙራት ኒያዞቭ ይባላሉ። ቱርክሜኒስታንን ለሁለት ዓስርተ ዓመታት ያህል አስተዳድረዋል - ገዝተዋል ቢባል የሚቀል ይመስለኛል። አነሳሳቸው ከዝቅተኛ ቤተሰብ ነው። አባታቸው ናዚ ጀርመንን ሲዋጉ እንደሞቱ ይነገራል። ሌሎቹ ቤተሰቦቻቸው ደግሞ በመሬት መንቀጥቀጥ ስለሞቱ ወላጅ አልባ ነው ሆነው ያደጉት። ብዙም ሳይቆይ ግን አገራቸው የሶቪዬት አንድኛዋ ክልል በነበረችበት ወቅት የኮሙኒስት ፓርቲው አባል በመሆን የቱርክሜን ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ሆነው ለዓመታት ሠርተዋል። በሶቪዬት ኅብረት ኮሙኒስታዊ አገዛዝ መለኪያ እንኳን ፓርቲያቸው ፈጽሞ ተሃድሶን የማያውቅ አምባገነናዊ እንደነበር ይነገራል። ሙሉውን አስነብበኝ ...