አቶ ስዬ አብርሃ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ አቶ መለስን ተቹ

Ato Siye AbrehaEthiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 26 ቀን 2000 ዓ.ም. June 3, 2008)፦ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ ያላቸውን አስተያየት ሰጡ። የድንበር ማካለሉን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠውን መግለጫ፣ በተለይም ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ለፓርላማው ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም. የሰጡትን ማብራሪያ አቶ ስዬ አብርሃ ተችተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅና ኃይሌ ገብረሥላሴ ቴዲ አፍሮን አነጋገሩት

ቴዲ አፍሮ በሽምግልና ሊለቀቅ ይችላል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 26 ቀን 2000 ዓ.ም. June 3, 2008)፦ ቅንጅቶችን በማስፈታት ሂደት ከፍተኛውን የሽምግልና ሂደት ያከናወኑት የሽማግሌዎች ሕብረት መሪና አባል የሆኑት ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅ እና ዝነኛው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ባለፈው ዓርብ በቃሊቲ እስር ቤት በመገኘት ቴዲ አፍሮን ያነጋገሩት መሆኑን ታማኝ የሆኑት የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

16 ዘይት መጭመቂያዎች ታሸጉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 26 ቀን 2000 ዓ.ም. June 3, 2008)፦ ከመርዛማ ዕፁ ጋር የምግብ ዘይት ቀላቅለው ሲያመርቱ የነበሩ 16 የዘይት መጭመቂያ ቤቶች መታሸጋቸውን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የድርጊቱ ፈፃሚዎች እስካሁን እንዳልተደረሰባቸውና ፋብሪካዎቹ ስለመታሸጋቸውም መረጃ እንደሌላቸው ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንዋይና ታማኝ በጋራ በስቶክሆልም የሙዚቃ ዝግጅት አሳዩ

 ንዋይ ደበበ በቅርቡ አዲስ ነጠላ ዜማ እንደሚለቅ ገለጸ

Neway Debebe & Tamagne Beyene, Stockholm, 20080530Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. May 31, 2008)፦ አርቲስት ንዋይ ደበበ እና ታማኝ በየነ በአንድነት በትናንትናው ምሽት በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ለርካታ ኢትዮጵያውያንና ለጥቂት የሌሎች ሀገር ዜጎች ሲያሳዩ አመሹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የታሰሩት የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች በዋስ ተለቀቁ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. May 31, 2008)፦ ትናንት ጠዋት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አራት ፖሊሶች ከቢሯቸው ተወስደው የታሰሩት ሁለት የ”አዲስ ነገር” ጋዜጣ አዘጋጆች ረፋዱ ከሰዓት ላይ በዋስ መለቀቃቸውን ከአዲስ አበባ የደረሰን ሪፖርት አስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"አንድነት" ፓርቲን የሚመሰርቱት የቀድሞ ላዕላይ ም/ቤት አባላት 18 ናቸው

አቶ ሙሉነህ ኢዮኤል እና ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ መሰብሰብ አቁመዋል

ሰኔ ሰባት ጠቅላላ ጉባዔው ይካሄዳል

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. May 30, 2008)፦ በሀገራችን የምርጫ እና የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በማይረሳው ምርጫ 97 ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ አግኝቶ የነበረው የ“ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ” አመራሮች እና የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ሲከፋፈሉ መሰንበታቸው አይዘነጋም። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አመራሮቹና የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላት አሁን በስተመጨረሻ ክፍፍሉ መስመር እየያዘና እየጠራ በመምጣት ላይ እንደሚገኝ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ም/ዋና አዘጋጅ ታሰሩ

አቶ አየለ ጫሚሶ አራተኛ ጋዜጣ ከሰሱ

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. May 30, 2008)፦ በየሣምንቱ ቅዳሜ መታተም ከጀመረ 32 ሣምንታትን ያስቆጠረው “አዲስ ነገር” ጋዜጣ በእነ አቶ አየለ ጫሚሶ ከሳሽነት በዛሬው ዕለት አዘጋጁና ም/ዋና አዘጋጁ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለኢትዮጵያ ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰው ዘገባ ያስረዳል። ከሳሻቸው አቶ አየለ ጫሚሶ መሆናቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገሌ ቦረና በሁለት ሆቴሎች በተወረወሩ ቦምቦች 3ሞቱ፣ 5 ቆሰሉ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ግንቦት 21 ቀን 2000 ዓ.ም. May 29, 2008)፦ ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረበትን 17ኛ ዓመት ባከበረበት ረቡዕ ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ከተማ በሁለት ሆቴሎች ላይ ተወርውሮ በፈነዳ ቦምብ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ቆሰሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...