ኃይማኖት፣ ፖለቲካ እና ግብረገብ (መክብብ ማሞ)

መክብብ ማሞ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው ግርግር የብዙዎቻችንን ቀልብ የሳበ መሆኑ ዕሙን ነው። ወደ ግርግሩ በመግባት ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት አልፈልግም - የሙያው ብቃትም ሆነ ዕውቀት የለኝም። ሆኖም ግን በዚህ ጽሑፍ ለማተኮር የፈለኩት ፍትህንና የሰብዓዊ መብትን በተመለከተ የኃይማኖት መሪዎች እስከምን ድረስ መሄድ ይጠበቅባቸዋል የሚለውን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ወጣት፡ ፈተናና ተስፋ፤ የኔ የርቀት እይታ

 ተክለሚካኤል አበበ

 (ክፍል ሁለት)

 

ሌላው እንደጠላቶቻችን ወይም እንደባላንጣዎቻችን የምንመለከታቸው ሰዎች ወደኛ ጎራ ሲያቀኑ ለመቀበልና በአባልነት ልንደባልቃቸው መዘጋጀት አለብን። ለምሳሌ ተስፋዬ ገብረአብን እንውሰድ (ስለዚህ ሰው ጉዳይ ከዚህ በፊትም ጭሬያለሁ)። አንዳንድ ሰዎች፡ በተለይ የድሮ የሻእቢያ ቂም ላይ ሙጭጭ የሚሉ ሰዎች፡ የተስፋዬ መጽሀፍ ምንም ሊዋጥላቸው አልቻለም።
 
ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ወጣት፡ ፈተናና ተስፋ፤ የኔ የርቀት እይታ

ተክለሚካኤል አበበ 

 “ውይይት ለሰላምና ለጋራ ዓላማ በኢትዮጵያ” ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የቀረበ ጽሁፍ

እንደመግቢያ፡ እንደ ዳራ

(ክፍል አንድ)

 ስለኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር መናገር እያዳገተኝ መጥቷል። መሰረታዊ ችግራችንን የሚያገዝፉት የጥቃቅን ችግሮች ስብስብ ከጠበቅነው በባሰ ፍጥነት ስለሚለዋወጡ ዋናው ችግር እንዲህ ነው፡ መፍትሄውም እንዲህ ይሁን ብሎ መናገር ቸግሯል። የዛሬ ስምንት አመት አገር ስለቅ ሶስት መቶ ብር ትቼው የወጣሁት ጤፍ ዛሬ አንድ ሺህ ገብቷል።

 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙሉዓለም ኢኮኖሚና የሉዓላዊነት ኢኮኖሚ (ፕ/ር መስፍን)

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም - ሰኔ 2001 ዓ.ም.

ሪፖርተር (ሰኔ 10 ቀን 2001 ዓ.ም.) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምዕራባውያን በእርዳታ አሰጣጣቸው የአፍሪካን ሀገሮች የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት አያከብሩም በማለት ንግግር ማድረጉን ዘግቧል። ከጥቂት ዓመታትኢ በፊት (ከሦስት ዓመት የሚበልጥ አይመስለኝም) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሙሉዓለም (ግሎባል) ሌላ አማራጭ የለም ብሎ መናገሩ ትዝ ይለኛል። የሙሉዓለም ኢኮኖሚ ማለት የሉዓላዊነት ኢኮኖሚ ማአለት ነው? ወይስ የሁለቱም ትርጉም በድንገት ተለወጠ? ለመሆኑ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ምን ማለት ነው?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንገቱን የደፋ ሩቅ ማየት አይችልም (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

ዳኛቸው ቢያድግልኝ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በአካልም ይሁን በሃሳብ አንገቱን የደፋ ሩቅ ማየት አይቻለውም። አንገታችንን ስንደፋ የዕይታችንን መጠን እናሳንሰዋለን፤ እንደ ቁመታችን ልክና እንደቆምንበት መሬት የምናየውም ይገደባል። በሞራልም በመንፈሥም አንገት ከደፋን ነገን የማየት አቅም ያንሰናል። ኑሮአችን የዛሬን ብቻ ይሆናል። ለዛሬ ብቻ መኖር ማለት ደግሞ ከሆድ እልፍ አይልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መለስ ለምን ሥልጣኑን መልቀቅ ፈለገ? (ብራና)

ብራና This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መለስ ዜናዊ ከፖለቲካ እና ከመንግሥት ሥልጣን እንደሚለቅ በተደጋጋሚ ገልጿል። በዚህ የመለስ ውሳኔ ላይ ጊዜ ሰጥቶ መወያየቱ ለተቃዋሚ ቡድኖች ጠቀሜታ ይኖረዋል የሚል ግምት አለኝ። በመለስ ሥልጣን መልቀቅ ዙሪያ ሦስት እንድምታዎች ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅርብ በሆኑ ተንታኞች እየተስተናገዱ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስ ብሔራዊ መግባባት አጀንዳችን ነው አሉ (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ - ሐምሌ 3 ቀን 2001 ዓ.ም.  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የአሥራ ሰባት ዓመት ወጣት ነው። ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ በእጁ ይዟል። እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ፣ ንግግር አድርገው ወደ ጨረሱ አንድ የዕድሜ ባለጸጋ ሰው ቀስ በቀስ ይጠጋል። ሳያስቡት የያዘውን ሽጉጥ ወደ እርሳቸው ደቅኖ ይተኩሳል። ሰውዬው ይወድቃሉ። አካባቢው ተረበሸ። ተናወጠ። አምቡላንስ ተጠርቶ በአፋጣኝ በስፍራው ደረሰ። የወደቁትን አባት በአምቡላንሱ የነበሩ የሕክምና ባለሞያዎች አነሷቸው። የፍጥነት ጉዞ ወደ ሆስፒታል ጀመሩ። ሆስፒታል ሳይደርሱ በመንገድ ላይ የኝህ ሰው ሕይወት አለፈች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ የራስዋን ፓትርያርክ የሾመችበት የ፶ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል

አብርሃም ሠሎሞን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የራስዋን (ኢትዮጵያዊ) ፓትርያርክ የሾመችበትን 50ኛ ዓመት በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ማክበሯ ይታወቃል። ”የዛሬ ሰማንያ ዓመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእራስዋ ልጆች ጳጳሳት ተሹሞላት ኃይማኖቷን በመጠበቅና በማስጠበቅ ብትኖርም፤ ከሁሉ የበለጠው ደስታ ግን የተፈጸመው የዛሬ ሃምሳ ዓመት ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፩ (ሰኔ 21 ቀን 1951) ዓ.ም. ከመጨረሻው ግብፃዊ አባት አቡነ ቄርሎስ በኋላ ከእራስዋ ልጆች መካከል የመጀመሪያ ፓትርያርኳን አቡነ ባስልዮስን ስትሾም ነው።” የሚለን አብርሃም ሠሎሞን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ ቁልፎች (በትረ ሙሴ)

በትረ ሙሴ  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“ከዘፀዐት በፊት” በሚለው ጽሑፌ ላይ ወደ ሀገራችን መመለስ አለብን፤ ነገር ግን ከዛ በፊት መንፈሣዊ ዝግጅት ያስፈልገናል ብዬ ነበር። ለዚህም አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦችን በዚች አጭር ጽሑፍ አቅርቤአለሁ። ርዕሱን “ኢትዮጵያዊ ቁልፎች” ያልኩበት ምክንያት በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተጠቀሱት ቀላል፤ ነገር ግን መሠረታዊ ነጥቦች እንደ እኔ ግምት ለችግራችን እንደ መክፈቻ ቁልፍ ናቸው ብዬ ፅኑ እምነት ስላደረብኝ ነው። አንብበናቸው የሚጠቅሙ ናቸው ያልናቸውን ልንጠቀምባቸው ግድ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቻለው ሁሉ አስተዋጽዖ ያድርግ እየተባለ ነው፤ እኔም በአቅሜ እነሆ ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ነጥቦች ታነቡልኝ ዘንድ በፍቅር እጠይቃለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከዘፀዐት በፊት (በትረ ሙሴ)

በትረ ሙሴ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የተወደዳችሁ ወገኖቼ!

ተደጋጋሚ ውድቀት፣ ውርደት፣ ስደት፣ መከራ፣ ችግር እና የመሳሰለት ነገሮች ለገጠመው አንድ ህዝብ በነገሮች ላይ እምነት ቢያጣ አይፈረድበትም። እኛ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ሰዓት የገጠመን ድክመት ይኼ ነው። እምነት የለንም። ስለዚህ ሁለ ነገር ጭልምልም ብሎ ይታየናል፤ ከዚያ ሁሉ ነገር ይበላሻል። ለማንኛውም ነገር ትዕግስት አስፈላጊ መሣሪያ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...