በክፍፍል የሚታመሰው የተቃዋሚዎች መንደር (ጽዮን ግርማ)
የፓርቲዎች አመራሮች ስለ ክፍፍሉ ይናገራሉ
ጽዮን ግርማ
ከተመሠረተ በአንድ ዓመቱ የመሰንጠቅ አደጋ ያንዣበበትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የነበሩና ያሉ ፓርቲዎችን በአንድነትና በሕብረት መሥራትና መጓዝ ያለመቻላቸውን አባዜ አስመልክቶ ጋዜጠና ጽዮን ግርማ በጉዳዩ ላይ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን፣ ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራውን፣ የፖለቲካ ምሁራንን፣ አቶ ገብሩ አስራትን፣ አቶ ስዬ አብርሃን እና ሌሎች ወገኖችን በማነጋገር ያቀረበችው ጽሑፍ ነው። መልካም ንባብ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...
መክብብ ማሞ ( 
"... ከሁለቱ የመጫወቻ ሜዳዎች ትይዩ ባለች አንድ ዛፍ ጥላ ስር በርጫና ሽሻው ሞቅ ብሏል። ለየት ባለ መልኩ “ለመዝናናት የመጡ” ወጣቶች ሕይወታቸውን ይቀጫሉ። ጫትን በግልጽ መቃምም ሆነ መሸጥ አይከለከልም። “ኢትዮጵያም አይከለከልም” ያለኝ ወዳጄን አልረሳውም። “ይህ የኢትዮጵያን ባህልም የምናንጸባርቅበት መድረክ ነው። ሀገራችን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም በግልጽ ነው የሚቅመው።” ነበር ያለው። እውነቱን'ኮ ነው። ለኳስ ከመጣው ለጫት የመጣው ይበልጥ ነበር። በዚሁ ከቀጠለ በቅርብ ጊዜ የስፖርቱ ፌዴሬሽን - የአውሮፓ የጫትና ሺሻ ፌዴሬሽን የማይሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ..." በማለት በፓሪስ የተካሄደውን በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫልን የገመገመው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ነው። 


