ሰማኸኝ በለው በነፍስ ማጥፋት ክሱ ይግባኝ ተጠየቀበት

Semahegn BelewEthiopia Zare (ኀሙስ መጋቢት 11 ቀን 2000 ዓ.ም. March 20,2008) ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው የዛሬ ስድስት ዓመት ሐምሌ 7 ቀን 1994 ዓ.ም. ከለሊቱ 10 ሰዓት ላይ አቶ ግሩም ተስፋዬ የተባለ ግለሰብን በቸልተኝነት በመኪና በመግጨት ባምቢስ ድልድይ ውስጥ በመክተት ነፍስ አጥፍተሃል ተብሎ ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤቱ ሦስት ሺህ ብር ቀጥቶ አሰናብቶት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የቦርዱን ውሳኔ ተጠባበቁ ተባለ

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2000 ዓ.ም. March 17,2008) የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመስራች አባላት ማሰባሰቢያ ቅጽ አሁንም በድጋሚ ላልታወቀ ጊዜ ቦርዱ ተሰብስቦ ምላሽ ይሰጣችኋል ተባለ። የምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ማመላለስ ህዝቡ ሁኔታውን በንቃት እንዲከታተለው በር ከፍቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዶላር መመንዘሪያ ቦታዎች በፓሊስ ተከበው ዋሉ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 6 ቀን 2000 ዓ.ም. March 15,2008) የዶላር ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ መናር ምክንያቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጥቁር ገበያ የዶላር መመንዘሪያ ሱቆች ናቸው በሚል ፖሊስ የመመንዘሪያ ቦታዎችን መቆጣጠሩ ተዘገበ። በአካባቢው መውጣትና መግባት አይቻልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ለሦስተኛ ጊዜ ተቀጠረ

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2000 ዓ.ም. March 14,2008) የመስራች አባላት የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅጽ እንዲሰጣቸው የጠየቁት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት ለሦስተኛ ጊዜ ለሰኞ መቀጠራቸው የምርጫ ቦርድ ሥርዓትን ያልተከተለ አሰራር ነው ሲሉ ታዛቢዎች አስተያየት ሰጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ አውቶቡስ ላይ ፈንጅ ፈንድቶ 8 ሰዎች ሞቱ 22 ቆሰሉ

"የሻዕቢያ እጅ አለበት" የኢህአዴግ ባለሥልጣናት

Ethiopia Zare (ኀሙስ መጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም. March 13,2008) ከሁመራ ከተማ ወደ መቀሌ ይጓዝ የነበረ 60 ሰዎችን በጫነ ሰላም በመባል የሚታወቅ የህዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ 22 ሰዎች መቁሰላቸውን ዛሬ አመሻሹ ላይ የደረሰን ዘገባ ጠቆመ።

"ሠላማዊ ትግል ብቸኛ አማራጭ ነው" አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ

ለአውሮፓ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ካውንስል የተጻፈ

Ethiopia Zare (ኀሙስ መጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም. March 13,2008) "ሠላማዊ ትግል ብቸኛው አማራጭ ነው" ሲል ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶችን በመዘርዘር በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው ቅንጅት (አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ) ፓርቲ ለአውሮፓ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ካውንስል በፃፈው ደብዳቤ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"አቶ በድሩ አደም ለወያኔ/ኢህአዴግ እውቅና ሰጡ" አስተያየት ሰጪዎች

Ethiopia Zare (መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008) "በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አምኖ የነበረው ዲያስፖራ እኔ እውነቱን ስነግረው አምኖ ተፀፀተ" ሲሉ አቶ በድሩ አደም ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ። "ወ/ት ብርቱካን የተመረጠችው ያለምንም ልምድ ኦሮሞና ሴት ስለሆነች ብቻ ነው" ሲሉም ተናግረዋል። አቶ በድሩ "ቅንጅት የጀመራቸውን ሥራዎች ኢህአዴግ ተግባራዊ እያደረጋቸው ነው" ማለታቸውን ተከትሎ ብዙዎች ለወያኔ/ኢህአዴግ እውቅና ሰጥተዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ማመልከቻውን ለምርጫ ቦርድ አስገባ

ለነገ ተቀጥረዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008) በቅንጅቱ ተ/ም/ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ የሚመራው ሥራ አስፈፃሚ አዲስ ለሚያቋቁመው ፓርቲ ሥም ከመረጠ በኋላ የፓርቲውን ሕጋዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችለውን ፊርማ ለማሰባሰብ የሚያስችለውን ቅፅ እንዲሰጠው በዛሬው ዕለት ለምርጫ ቦርድ አመለከተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...