የጉጂ ኦሮሞና አማሮ ኬሌ በተነሳ ብጥብጥ ከ20 በላይ ሰዎች ሞቱ

የብሔር ግጭት በኢትዮጵያ ተባብሷል

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008) ባለፈው ሣምንት በደቡብ ክልል በተነሳ በጉጂ ኦሮሞ እና አማሮ ኬሌ በተባሉ ብሔረሰቦች መካከል በተነሳ ብጥብጥ ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውን በአካባቢው ያሉ ምንጮች ገለፁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በገዳማይቱ ፌዴራል ፖሊስና ኢሣዎች ተጨፋጨፉ

Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. March 10,2008) በአፋር ክልል በምትገኘው ገዳማይቱ በተባለችው ኬላ ላይ በኮንትሮባንድ ንግድ ምክንያት በኢሣዎች እና በፌዴራል ፖሊስ ምክንያት በተነሳ ብጥብጥ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች ከሁለቱም ወገን መሞታቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቅንጅት ሥራ አስፈጻሚ የፓርቲውን አዲስ ስም ሰየመ

(ሰበር ዜና)

 

Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 30 ቀን 2000 ዓ.ም. March 9,2008) በብርቱካን ሚደቅሣ የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከላእላይ ም/ቤት በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት ዛሬ ለቅንጅት አዲስ ስያሜ መስጠታቸውን ታማኝ ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አምስት ጋዜጠኞች ተከሰሱ

ሦስቱ ታስረው፣ ቃላቸውንና አሻራ ሰጥተው በዋስ ተለቀቁ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2000 ዓ.ም. March 8,2008) "ፎርቹን" የተሰኘው በኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩረውና በየሣምንቱ ዕሁድ እየታተመ የሚወጣው ጋዜጣ አምስት አዘጋጆች ተከሰሱ። ጋዜጣው ስሜን አጥፍቶ ኪሳራ አድርሶብኛል ሲል በድጋሚ የከሰሳቸው አያት አክሲዮን ማኅበር መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትላንት አንድ ብር ከሃያ አምስት የነበረ ጨው ዛሬ ከ7-12 ብር ገባ

ሠላሳ ነጋዴዎች ታሰሩ

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 28 ቀን 2000 ዓ.ም. March 07,2008)፦ በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገና የአላቂና የጥቃቅን እቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የዋጋ ንረት እያሳዩ ከመሆዩም በላይ ትላንትና አንድ ብር ከሃያ አምስት ይሸጥ የነበረ የአንድ ኪሎ ጨው ዋጋ እንደየአካባቢው የሽያጭ ዋጋ ከ7 ብር እስከ 12 ብር እየተሸጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእነ ዳንኤል የይግባኝ አቤቱታ ለመጋቢት ተቀጠረ

Daniel & NetsanetEthiopia Zare (ዓርብ የካቲት 28 ቀን 2000 ዓ.ም. March 07,2008)ከቅንጅት አመራሮች ጋር ታስረው እስከ አሁን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ሁለት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አባላት አቶ ዳንኤል በቀለና አቶ ነፃነት ደምሴ "ጥፋተኛ ተብለን ልንቀጣ" አይገባም በሚል ያቀረቡት አቤቱታና ዐቃቤ ደግሞ "ጥፋተኛ ተብለው የተቀጡበት አንቀፅ አንሷል፤ በዕድሜ ልክ እስራት ሊቀጡልኝ ይገባል" በሚል ያቀረበው የይግባኝ ማመልከቻ በተለያየ መዝገብ ለመጋቢት ወር ተቀጠረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሮፌሠር መስፍን ፊርማ ሊያሰባስቡ ወደ አማራ ክልል ይጓዛሉ

የምርጫ ቦርድ ምላሽ ነገ ይጠበቃል 

Ethiopia Zare (ኀሙስ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም. March 06,2008) ከእስር የተፈቱት የቀድሞው ቅንጅት //ሊቀመንበር / ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ 12 አባላት አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁሙ መሆኑን በመግለፅ ፊርማ ለማሰባሰብ የሚያስችላቸውን የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሰጣቸው በትናንትናው ዕለት ለምርጫ ቦርድ ያመለከቱ ሲሆን፣ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም ለአዲሱ ፓርቲ ፊርማ ለማሰባሰብ ወደ አማራ ክልል እንደሚጓዙ ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ጠቆመ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳዊት ከበደ ዛሬ በዋስ ተለቀቀ

‘ክሱ አስቂኝ ነው’ ታዛቢዎች

Ethiopia Zare (ኀሙስ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም. March 6, 2008)፦ ዛሬ በደረሰን ሰበር ዜና መሰረት ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የተከሰሰው የአዲሱን "አውራምባ ታይምስ" ጋዜጣ ማስታወቂያ በአንድ የኢህአዴግ ተመራጭ ማስታወቂያ ላይ ለጥፈሃል በሚል ሲሆን፣ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ቤቱ በዋስ እንደለቀቀው ለማወቅ ችለናል። ከሳሹ ምርጫ ቦርድ እንደሆነ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...