የገብረመድህን ወግ (ልጅ ተክሌ)

ልጅ ተክሌ ነኝ ከቫንኩቨር ካናዳ

“ኢትዮጵያውያን (በተለይ አማሮች) ቢኖሩ አይጠቅሙንም፤ ቢጠፉም አይጎዱንም” ህወሓት1975 ዓ.ም.

እየተጓዝኩ ነበር። ከቦታ ቦታ። ከቢሲ እስከ ዲሲ የታዘብኩትን፣ የከነከነኝን፣ ሆዴን የበላውን እጽፋለሁ እያልኩ ስዘገጃጅ በዚህ መሃል ነው ገብሬን ሲናገር የሰማሁት። ገብረመድህን አርኣያ። የሱ ወግ ጊዜ አልሰጠኝም። ሌላው ይቆይ። የቀድሞ የህወሓት አባልና ገንዘብ ቤትን ወግ ላወጋችሁ ፈቀድኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የባንዲራው ምስጢር በፓሪስ (ይንበርበሩ ደምሴ)

ይንበርበሩ ደምሴ

ሰባተኛው በአውሮፓ የስፖርትና የባሀል ፌስቲቫል ዝግጅትን በተመለከተ 3 የተለያዩ ፀሐፊዎች (2 ከስዊዘርላንድ፣ አንድ ከሆላንድ) የጻፉትን አስተያየት ካነበብኩ በኋላ፤ በዓሉ ላይ የታዘብኩትንና ሦስቱ የተለያዩ ፀሐፊዎች እንደዋዛ የረሱትን የባንዲራውን ምስጢር ለመጻፍ ወሰንኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ አፍሮ ተፈታ - አንድ ብለናል፤ ብርቱካን ትቀጥል! (ግርማ ካሣ)

Hale Mideksa, W/t Birtukan's daughterTeddy Afroግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) ነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ.ም.

ሰሞኑን የተፈጠረውን ክስተት ከግምት ውስጥ በማስገባት ኅዳር 24 ቀን 2001 ዓ.ም.፣ “የቴዲ አፍሮ መታሰር በኢትዮጵያዊነት ላይ ያነጣጠረ ነውን?” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ጽሑፍ አሻሽዬ እንደሚከተለው ለአንባብያን አቅርቤዋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መቆጣት ያቃተው ወይስ … ህዝብ (ዳናቸው ቢያድግልኝ)

መቆጣት ያቃተው ወይስ ቁጣውን ወደ ተግባር መለወጥ የተሳነው ህዝብ

Funeral; A woman carries the body of a child who died of malnutrition.ዳኛቸው ቢያድግልኝ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በሀገራችን የተለመደው በደስታም ይሁን በኀዘን አብሮነት ነበር። እኒህ የፎቶ መረጃዎች ግን የሚያመለክቱት አስተዛዛኝም ጭምር የጠፋበትና ልጅን በብርድልብስ ጠቅልሎ ብቻውን ወደ ቀብር መሄድን ነው። ይህ ዝነኛውና አረንጓዴው ረሃብ በመባል የሚታወቀውና በተለይ በደቡብ ክልል ያለውን ህዝብ እያጠፋ ያለው ምርት አልባነት ነው። በለምለሙ መስክ ላይ የእህል ክምር ሳይሆን የሕፃናት ሬሳ የሚቆለልበት የሀገራችን ክፍል መሆኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምኅዳር በስቱድዮ እና ምኅዳር በአዳማ (ስየ አብርሃ)

ስየ አብርሃ

እሁድ ነሐሴ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ እንዲገኙ ከተጋበዙት የመድረክ ለዲሞክራሲ ምክክር በኢትዮጵያ (መድረክ) አባላት አንዱ በመሆን ወደ አዳማ ሄጄ ነበር። እንደ እኔ ሁሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፌሠር በየነ ጴጥሮስ፣ አቶ ቢንያም ሄራቦ እና አቶ ሃዲ መሐመድ በእንግድነት ተገኝተዋል። የመድረኩ አባል የኾኑ ፓርቲዎች በሚጠሩዋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ጉባዔዎች ስገኝ የመጀመርያዬ አይደለም። በተናጠል የሚደረግ ትግል ብዙ ርቀት እንደማያስኬድ፤ ገዢው ፓርቲ የሚያደርሰውን አፈና ተቋቁሞ ውጤታማ ሥራ መስራት የሚቻለው ትግልን አስተባብሮ በመሄድ ብቻ መኾኑን ከመገንዘብ የተፈጠረ መድረክ እንደመሆኑ የመድረኩ አባል ፓርቲዎች በሚጠሩዋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ስገኝ ቆይቻለሁ ወደ ፊትም እቀጥልበታለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቴዲም በህዝብ ላይም “መትፋት” ያስነውራል! (ልዑልሰገድ)

ልዑልሰገድ (ከአቢሲኒያ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“ማንም ሰው ከሕግ በላይ አይደለም” ይሄን ማለቱን የሰማነው አንድ የሕግ የበላይነት ባለበት ሀገር የሚሠራ እና እውነተኛ ዳኛ ቢሆን አያስገርምም ነበር። እንዲህ የተባለውም በሕግ ፊት ከፍርድ በፊት ንፁኅ ሆኖ የመገመት መብቱ ታውቆ፣ በነፃ የመከራከር መብቱ ተጠብቆ፣ ሁሉም ማስረጃዎቹ ተመዝነው ፍትህ ለተሰጠው ሰው ቢሆን ዜና መሆኑ ይቀራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛዋ ብርቱካንስ? (ፍቅሩ ይበልጣል)

W/t Birtukan Mideqssa ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳፍቅሩ ይበልጣል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

መደበኛ የሥራ ሰዓቴን ጨርሼ እንደተለመደው ወደቤቴ አመራሁ። የቤቴን በር ከፍቼ ስገባ ልጆቼ ተሯሩጠው የተለመደ አቀባበላቸውን ካረጉልኝ በኋላ እኔም ሳም ሳም አድርጌያቸው ሁሌም አረፍ የምልበት ሶፋ ላይ ዝርግፍ ብዬ ቁጭ አልኩ። ዘወትር የምገባበት ሰዓት የምሽቱ ዜና የሚሰማበት ጊዜ በመሆኑ የቴሌቪዥኑን ጣቢያ መቀያየሪያ አንስቼ የዕለቱ ዜና የሚገኝበት ላይ ለመቀየር መነካካት ጀመርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኃይማኖት ወይስ የፖለቲካ ቀውስ (እውነቱ ዘገየ)

እውነቱ ዘገየ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

“ሕመሙን የደበቀ ፈውሱን ደበቀ” እንደሚባለው የችግሮቻችን መንስዔዎች በቅጡ ተለይተው መታወቃቸው ድልን የመቀዳጀት ያህል የሚፈጥርብን ደስታና ስሜት ባይፈጥሩልንም ውለው አድረው የሚያመሩን ወደዛ ሃሴት ነው። ቅድስት ቤ/ያን ለዚህ ቀውስ የዳረጋትን የችግሮችዋን መንስኤዎች ቀጥተኛ በሆነ መልኩ (መንገድ) ከግላዊ አጀንዳዎችንና አስተሳስባችን ርቀን ጭብጥ ባላቸው መረጃዊ በሆነ ውይይት እንደ ባለ አዕምሮ በጭዋነት መንፈሥ በመጠባበቅ አንስተን መወያየቱና ለመፍትሔ መደማመጡ ዘለቄታ ያለው ሠላምና እረፍት ያመጣል የሚል እምነት አለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያለ ምርጫ ተቋም እንዴት ስለ ምርጫ እናወራለን? (ልዑል ሰገድ)

ልዑል ሰገድ (ከአቢሲኒያ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ ሰብሳቢን ስለ ምርጫ አንዳንድ መረጃዎች ለመጠየቅ ከቢሯቸው በር ላይ እጠብቃለሁ። አቶ ከማል በድሪ የቦርዱ ሊቀመንበር፣ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት፣ የሕገ-መንግሥት አጣሪ ጉባዔ አባልም ናቸው። በተሰጣቸው ሥልጣን ከሳቸው በላይ ስለ ምርጫው ሊጠየቅ የሚገባው የለም ብዬ ነበር የግድ እሳቸውን ለማግኘት ደጅ የጠናሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግምገማው ሲገመገም (ምሥጢረ ኃይለሥላሴ)

7ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ውድድር በፓሪስ

ምሥጢረ ኃይለሥላሴ

ላለፉት አምስት ዓመታት በአውሮፓ የኢትዮጵያውያንን የእግር ኳስ ውድድር ተከታትያለሁ። ለEthiosports.comም ሪፖርቶችን፣ ዘገባዎችን ከግምገማ ጋር አቅርቤያለሁ። በአብዛኛው ብዙም ያልተቀየረ ቢሆንም የተመልካች ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ መታየቱ ለዕድገቱ መለኪያ ነው ከተባለ ዕድገት አሳይቷል ማለትም ይቻላል። በየዓመቱ ጉድለቶችን የምንጠቁመው በሚቀጥለው እንዳይደገም ለማድረግ ቢሆንም አልሰመረልንም። ዕድገት ታይቷል ሲባል ያልተፈለገውና እንዲታረም የተፈለገውም በዚያው መልኩ አድጓል ማለት ሊሆን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...